የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኮማንደሮችን ስራ መልቀቅ በተመለከተ ለኢሳት ዘገባ መልስ ሰጠ

ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽኑ መልሱን የሰጠው ኢሳት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኪሚሽነር ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁና የምዕራብ ጎጃም ዞን የወንጀል ምርመራ ሃላፊ የነበሩት ኮማንደር በላይ ካሴ ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በማስመልከት ዘገባ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሽብር ማህበራዊ ሚዲያ አራማጆች የአማራ ክልል ኪሚሽን ስራ ባልደረባ የሆኑት ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁና ኮማንደር በላይ ...

Read More »

በማእከላዊ ዜጎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው

ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት ሸራተን እየተባለ በሚጠራው የእስር ቤቱ ክፍል የሚገኝ ዘርኣይ አዝመራው የሚባል ከደባርቅ አካባቢ የመጣ ወጣት አባትህ ሸፍቷል በሚል በአሌክትሪክ “ ሾክ” ስለተደረገ ሰውነቱ እንደሚንቀጠቅ፣ በራሱ መሄድ ባለመቻሉም በድጋፍ እንደሚጓዝ ታውቋል። ሌሎችም በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች ተይዘው የመጡ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ ድብደባ የተፈጸመባቸው በመሆኑ ለአካል ጉዳት ተደርገዋል። አእምሮን በሚጎዳ ...

Read More »

አንድ ሺህ 438ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በመላው አለም ተከበረ

ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009) በአዲ አበባ ታላቁ አንዋር መስጊድና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተከበረው የኢድ አልፈጥር በአል ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጥር በተገኙበት ዩ ኤስ አሜሪካ በተለይም በዋሽንግተን ዲሲ በደማቅ ስነ-ስርዓት መከበሩን ዜናው ያስረዳል። የፈርስት ሂጂራ ፋውንዴሽን ኢማም ሼህ ካሊድ ኡመር እና የፋውንዴሽኑ ፕሬዝዳንት ሃጂነጂብ መሃመድ በተገኙበት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ ቨርጂኒያ ግዛት በተከበረው የኢድ አልፈጥር በአል ሙስሊሙ ማህበረሰብ በብዛት መገኘቱም ታውቋል። በከፍተኛ ...

Read More »

የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አጽም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል አረፈ

ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009) በርካታ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም አድናቂዎቻቸው በተገኙበት እሁድ ረፋድ ላይ በተካሄደው ስነ- ስርአት የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አመራሮች ታዋቂ ሰዎች መታደማቸውም ተመልክቷል። የታዋቂው የህክምና ባለሙያ የመኢህድ መስራችና ፕሬዝዳንት የነበሩት የፕሮ/ር አስራት ወልደየስ መካነ- መቃብርና ሃውልት ላለፉት 18 አመታት ከነበረበት ባለወልድ ቤተክርስቲያን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እንዲነሳ መወሰኑ ቁጣ መቀስቀሱ ይታወቃል። እሁድ ሰኔ 18/2009 ፍልሰተ አጽማቸው በመንበረ ጸባኦት ...

Read More »

የመውጫ ቀነገደቡ ቢያበቃም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ከሳውዲ አለመውጣታቸው ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009) የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን የውጪ ሐገር ዜጎች ሀገር ለቀው አንዲወጡ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ቢጠናቀቅም ከመቶ ሺዎች በላይ ኢትዮጵያዊያን ከሳውዲ አንዳልወጡ ህወሐት መራሹ መንግስት አመነ ። የጉዞ ሰነድ ከወሰዱት ወደ አገር ቤት የተመለሱት ከ 42 በመቶ በታች ነው።  የሳውዲ ኣረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን 2009 አ/ም ጀምሮ በነበሩበት ተከታታይ ሶስት ወራት ሕጋዊ የመኖሪያ ...

Read More »

የታዋቂው ገጣሚ ሻለቃ ክፍሌ አቦቸር አራተኛው የስነ-ግጥም መጽሃፉ ተመረቀ

ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009) “ሚስጥሯን-ያልገለጠልን” በሚል ርእስ በ175 ገጽ እና 61 የግጥም መድብሎችን የያዘው የስነ-ግጥም መጽሃፍ ቅዳሜ ሰኔ 24 ቀን 2017 በቨርጂኒያ አርሊንግተን የተመረቀ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የደራሲው ወዳጆችና አድናቂዎች እንዲሁም በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።  በምረቃው ዝግጅት ላይ “ትላንትን ማስታወስ፣ ነገን ማሰብ ካልተቻለ የዛሬ ፈተና አይተላለፍም” በማለት የእንኳን ደህና መጣችሁ የመግቢያ ንግግር ያደረገው የመጽሃፉ ደራሲ ሻለቃ ክፍሌ አቦቸር ...

Read More »

በሶማሌ ክልል ህጻናት በረሃብ እየሞቱ ነው ሲል ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ይፋ አደረገ

ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን በያዝነው ሰኔ ወር ብቻ 67 ሕጻናት በረሃብ መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ሰኞ ይፋ አደረገ። 51 ህጻናት የሞቱት ወሩ በገባ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሆነም ተመልክቷል።  በኢትዮጵያ ሶማሌ ዞን ያለው የረሃብ ሁኔታ አስደንጋጭ ሆኖ መቀጠሉን ያስታወቀው የፈረንሳይው ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን 27 የመመገቢያ እንዲሁም አራት የህክምና እና የመመገቢያ ጣቢያ በማቋቋም ...

Read More »

የኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ሠራተኞች በቻይናውያን አሠሪዎቻቸው ድብደባ ደረሰባቸው

ሰኔ ፲፱( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሀዋሳ የቻይናውያን ኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሠራተኞች በቻይናውያን አሰሪዎቻቸው የከፋ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው በተለይ ለኢሳት ገለጹ። የፕሮጀክቱ ሠራተኞች እንደገለጹት በአሰሪዎቻቸው የከፋ ድብደባ የተፈጸመባቸው ላለፉት ወራት ያልተከፈላቸውን ደመውዝ እንዲከፈላቸው በጋራ ጥያቄ በማቅረባቸው ነው። “የሠራንበት የላባችን ዋጋ ሊከፈለን ይገባል። የሠራንበትን ደመወዝ ባለማግኘታችን ቤተሰቦቻችን ችግር ላይ ወድቀዋል” በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም ...

Read More »

በምስራቅ ኢትዮጵያ በምግብ እጥረት የተጠቁ ሕጻናት አስር እጥፍ መጨመሩን እና 67 ሕጻናት በርሃብ መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ

ሰኔ ፲፱( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ በኦጋዴን ዶሎ ዞን ያለው የርሃብና ያልተመጣጠነ ምግብ እጥረት አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን በአካባቢው የተሰማራ የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ። ”ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ በዶሎ ዞን ነዋሪ የሆኑ ታዳጊ ሕጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋላጭ ሆነዋል። የሕክምና ቡድናችን ባለፉት አስር ዓመታት በአካባቢው የሥራ ቆይታችን እንደዚህ ዓይነት ዘግናኝ ...

Read More »

አቶ ንዋይ ገብረአብ ለአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽነርነት ታጩ

ሰኔ ፲፱( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃቱ ባለስልጣን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅትን እንዲመሩ በተመረጡ 2 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፣ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ አቶ ንዋይ ገብረአብን ለአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ቦታ በእጩነት አቅርቧል። የአፍሪካ ህብረት ሹመት በመንግስታት ድጋፍ የሚገኝ በመሆኑ፣ አቶ ንዋይ ቦታውን የመውሰድ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ህወሃት አዲስ አበባ በገባ በአመቱ የአቶ ...

Read More »