የብአዴን መሪዎች የጎንደርን ህዝብ በማባበል ስራ ላይ ቢጠመዱም አልተሳካለቸውም

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህዝባዊ አመፁ ከተቀሰቀሰ እና አስቸኳይ አዋጅ ከታወጀ በኃላ ባሉት አራት ወራት ጊዜ ውስጥ ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ፣ የመከላከያ ሹማምንት ፣ የክልል ፕሬዝዳንቶች ፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ሌሎችም የኢህአዴግ አመራሮች በጎንደር እየተገኙ እራሳቸውን እየሰደቡ፣ ችግሮችን ለመፍታት ሲምሉ እና ሲገዘቱ ቆይተዋል። ለምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን አራተኛ መድረክ፣ ...

Read More »

ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው የታሰሩ 63 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ለኢህአዴግ መንግስት ተላልፈው ተሰጡ

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባሳለፍነው ሳምንት ሱዳን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት በሰላማዊ መንገድ ሕጋዊ መብቶቻቸውን የጠየቁ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ በኤንባሲው ፈቃጅነት በሱዳን የጻጥታ ኃይሎች ድብደባ፣ የጅምላ እስራት፣ አካላዊ ጥቃቶች መፈጸሙ እና አንድ ስደተኛም በስለት ተወግተው መገደላቸው ይታወቃል:: በሱዳን የፀጥታ ሃይሎች ተይዘው በተጨናነቀ በእስር ቤት ታጉረው የተለያዩ ሰቆቃ ሲፈፀምባቸው ከነበሩት ስደተኞች ...

Read More »

ገዥው ፓርቲ በፈጠረው ጫና ላለፉት አስር ቀናት ተቋርጦ የነበረው የኢሳት ቴሌቪዥን ስርጪት ዳግም ተጀመረ።

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ሀሳቦችን እንዳይሰማ ካለው ሥጋት በመነሳት እንደተለመደው ሁሉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሠስ የኢሳት ቴሌቪዥን ከአየር ላይ እንዲወርድ አድርጎ ቢሰነብትም ኢሳት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ዳግም ወደ አየር ተመልሷል። ቀደም ሲል ኢሳትን ሲከታትተሉ የነበሩ አድማጮች የዲሽ ሰሀን አቅጣጫ መቀየር ሳያስፈልጋቸው በፍሪኩዌንሲ Tel Star 12 Frequency 12738 Horizontal ...

Read More »

የኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነትና መረብ ኤጀንሲ የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን አስኮ ከተባለ ኩባንያ ለመግዛት የ1.3 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ፈጸመ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2009) መቀመጫውን በአውሮፓ ፖላንድ ያደረገ አንድ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ለኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነትና መረብ ኤጀንሲ የተለያዩ የኢንተርኔት የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ የ1.3 ሚሊዮን ዶላር (ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ) ስምምነት ፈጸመ። አስኮ (ASSECO) ግሩፕ የሚል መጠሪያ ያለው ይኸው ኩባንያ የረቀቁ የቴክኖሎጂ ሶፍትዌሮችን በማምረት ለተለያዩ ድርጅቶችና አገራት የሚያቀርብ እንደሆነ ኩባንያው በድረገጹ ላይ ካሰፈረው መረጃ ለመረዳት ተችሏል። የኢትዮጵያ መረጃና ደህንነት ...

Read More »

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጉዳይ ሲመለከቱ የነበሩት ዳኛ ቢሚያም ዮሃንስ በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አባላት ታፍነው መወሰዳቸው ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2009) የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጉዳይ ሲመለከቱ የነበሩ የጎንደር ከተማ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ዳኛ የሆኑት አቶ ቢኒያም ዮሃንስ ትላንት ማክሰኞ ከመስሪያ ቤታቸው በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አባላት ታፍነው መወሰዳቸውን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። ከወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጋር በተገናኛ የኮሚቴው አባል የሆኑትን እና በእስር ላይ የሚገኙትን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የክስ ጉዳይን በመዳኘት ላይ የነበሩ ዳኛ ቢኒያም በከተማዋ ...

Read More »

በኢትዮጵያና ሶማሊያ በድርቅ ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ የተጋለጠ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ አለም አቀፍ ጥሪ ቀረበ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያና ጎረቤት ሶማሊያ በድርቅ ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ የተጋለጠ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪን አቀረቡ። መቀመጫቸውን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ከተማ ያደረጉ የድርጅቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪዎች በሁለቱ ሃገራት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሞት እና የጤና አደጋ ውስጥ መሆናቸውን እንደገለጹ ሮይተርስ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ...

Read More »

ወደ ታንዛኒያ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ስጋት እየሆነ መምጣቱን የታንዛኒያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት አስታወቁ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2009) የታንዛኒያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ስጋት እየሆነ መምጣቱን ረቡዕ አስታወቁ። በዚሁ ድርጊት ተሳትፈዋል የተባሉ 13 ኢትዮጵያውያን ሰኞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ታንዛኒያ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን አክለው ገልጸዋል። ከአንድ ወር በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ሃገሪቱ ገብተዋል የተባሉ 83 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ...

Read More »

የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት መንግስት ከአለም-አቀፍ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት አባነት ለመውጣት ያሳለፈውን ውሳኔ ውድቅ አደረገ

ኢሳት (የካቲት 15 ፥ 2009) የደቡብ አፍሪካ መንግስት ከአለም አቀፍ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት አባልነት ለመውጣት ያስተላለፈውን ውሳኔ የሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ረቡዕ ውድቅ አደረገው። የደቡብ አፍሪካ መንግስት መቀመጫውን ዘ-ሄግ ዘ-ኔዘርላንድስ ያደረገው ፍርድ ቤቱ ፍትሃዊ የሆነ አካሄድ በአህጉሪቷ ላይ አይከተልም በማለት ከፍርድ ቤቱ አባልነት ለመሰናበት ከወራት በፊት ውሳኔን አስተላልፎ እንደነበር ይታወሳል። ይሁንና የሃገሪቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መንግስት ...

Read More »

ብሪታኒያ ለአፍሪካ አገራት የምትሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት ለሚደረግ እቅድ ማስፈጸሚያነት እንዲውል ጥያቄ ቀረበ

ኢሳት (የካቲት 14 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተወሰኑ የአፍሪካ ሃገራት የሚሰጠውን አመታዊ የገንዘብ ድጋፍ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት እያካሄደ ላለው እቅድ ማስፈጸሚያ እንዲያውለው የሃገሪቱ ሚኒስትሮች ጥያቄን አቅረቡ። ለአፍሪካ የሚሰጠው ድጋፍ እንዲታጠፍ ጥያቄን እያቀረቡ ያሉ የብሪታኒያ ሚኒስትሮች ሃገራቸው ድጋፍን በምስራቅ አውሮፓ ከሚገኙት ፖላንድ፣ ሃንጋሪ እና የባልቲክ ሃገራት (ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያና፣ ሊቶኒያ) ድጋፍ እንዲውል ጥያቄን አቅርበዋል። የብሪታኒያ መንግስት በየአመቱ 12 ቢሊዮን ፓውንድ ...

Read More »