ሟቹ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን አስጨፋሪ ከጨጓራ ህመም ውጪ ምንም ዐይነት ህመም እንደሌለበት ወላጅ አባቱ ገለጹ።

ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዘነበ አባት አቶ በላይ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት ልጃቸው ከጨጓራ ህመም ውጪ የልብ ድካምም ሆነ ድንገት ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ እንዳልነበረበት ጠቅሰው፤ እስካሁን ድረስ ምን ሆኖ እንደሞተ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በሀዘን ስሜት ተውጠው ተናግረዋል። ቡና ከሃዋሳ ከነማ ጋር ላለው ግጥሚያ ከአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን በፊት ወደ ሃዋሳ ሲያመራ አብሮ እንደተጓዘ ...

Read More »

አሜሪካ ለኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ አቋረጠች

ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2009) አሜሪካ ለኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የምትሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ለሙስና የተጋለጠ ነው በማለት ድጋፏን አቋረጠች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴት ለኬንያ መንግስት ባሳወቀው በዚሁ ውሳኔ 12 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ድጋፍ እንዲቋረጥ መደረጉን እንደገለጸ ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ማክሰኞ ዘግቧል። በኬንያ የአሜሪካ አምባሳደር ሮበርት ጎዴክ በሃገሪቱ ሙስናና ተጠያቂነት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ለኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በቀጥታ የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ...

Read More »

በህገወጥ መንገድ ወደ ሞዛምቢክ የገቡ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2009) የሞዛምቢክ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ 24 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ማክሰኞ አስታወቁ። ለቀናት ያህል በሃገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ስር የነበሩት ኢትዮጵያውያን ከአዲስ አበባ ሲነሱ የተሳሳተ ቪዛን ይዘው እንደተጓዙ የሞዛምቢክ የጸጥታ ሃላፊዎችን ዋቢ በማድረግ ዴይሊ ኔሽን የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ባለፈው ወር በተመሳሳይ መልኩ ወደ ሃገሪቱ ገብተዋል የተባሉ 13 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ያልተመጣጠነ የዜጎች ገቢን በማስመዝገብ በአለም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2009) ከ90 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላት ኢትዮጵያ በአለም ካሉ ሃገራት መካከል ያልተመጣጠነ የዜጎች ገቢን በማስመዝገብ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መፈረጇ ተገለጸ። ሃገሪቱ ባለፉት 10 አመታት የባለ ሁለት አህዝ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን አስመዝግባለች ቢባልም፣ ኢትዮጵያ አሁንም ድረስ በድህነት ውስጥ ከሚገኙ ሃገራት ተርታ አንዷ መሆኗን ወርልድ ኢኮኖሚስ ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያን አማካኝ የነፍስ ወከፍ ...

Read More »

ከህወሃት መሪዎች ጋር በሽርክና የሚሰሩ የሌላ አካባቢ ተወላጅ ጥቂት ባለሃብቶች ከፍተኛ ብድር እየወሰዱ መሆናቸው ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2009) ለኤፈርትና ለትግራይ ተወላጆች ከሃገሪቱ ባንኮች ከፍተኛ ሃብት በብድር መውጣቱ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት፣ ከህወሃት መሪዎች ጋር በሽርክና የሚሰሩ የሌላ አካባቢ ተወላጅ ጥቂት ባለሃብቶች በተመሳሳይ ከፍተኛ ብድር እየወሰዱ መሆናቸውን ምንጮች ገለጹ። በሌላ በኩል በንግዱ አለም በራሳቸው ጥረት ውጤታማ የሆኑት ሲገፉ መቆየታቸውና አሁንም በመገፋት ላይ መሆናቸውንም ኢሳት ያጠናከረው ማስረጃ ያስረዳል። በተለይ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ብድር በመውሰድ ዕዳቸው ...

Read More »

በርካታ የኦሮሚያ ስፍራዎች ወደ ሶማሌ ክልል መጠቃለላቸውን የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት በግልጽ ተናገሩ።

ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጭናክሰንና በባቢሌ ከፍተኛ ውጥረትና ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች ትጥቅ እንዲፈቱ ተደርጓል። በኦሮሚያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢዎች ይፈጠሩ የውነበሩ ግጭቶች እልባት እንዳገኙ በቅርቡ በመንግስት መገናኛ ብዙሀን በተደጋጋሚ ቢገለጽም ሁኔታው ወደ አደገኛ መንገድ እያመራ እንደሆነ የባቢሌና የጭናክሰን ነዋሪዎች በተለይ ለኢሳት ገልጸዋል። የሶማሌው ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ እሁድ ዕለት በመከላከያ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት የኢትዮጵያ አማጽያንን ማሰራቸው ተዘገበ

ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው የደቡብ ሱዳን የደህንነት ባለሥልጣናት ጁባ ውስጥ የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር አባላት እንደሆኑ የሚታመኑ ስድስት አማጽያንን አስረዋል። ኢትዮጵያውያን አማጽያኑ የታሰሩት የአካባቢው ሚሊሻዎች ከሚጠቀሙባቸው ህገ ወጥ የመሣሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘ ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ለኢትዮጵያ መንግስት እጃቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር መሪ ጄነራል ቶዋት ፓል ቾይ የድርጅቱ ...

Read More »

ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖምን የሚቃወም ታላቅ አውሮፓ አቀፍ ሰልፍ ተጠራ

ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህዝባዊ ወያነ ኃርነት ትግራይ ዋና የሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት መመረጥ የለባቸውም ያሉ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታላቅ አውሮፓ አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አስታወቁ። እንደ ሰልፉ አስተባባሪዎች ገለጻ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት በሚደረገው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ...

Read More »

አስር ሚሊዮን ዶላር ወይም 230 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የኢትዮጵያ በርበሬ ጥራቱን ያልጠበቀ ነው ተብሎ ከአውሮፖ ተመለሰ።

ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሳምንታዊው ካፒታል እንደዘገበው ከፍተኛ መጠን ያለው ይህ የተፈጬ በርበሬ ከአውሮፓ ገበያ ሊመለስ የቻለው፤ በአውሮፓ መግቢያ ባሉ ላቦራቶሪዎች በተደረገ ምርመራና ቁጥጥር አፍላቶክሲን እና ኦክራቶክሲን የተባሉ በካይ ንጥረ ነገሮች ስለተገኙበት ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ በርበሬው የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ እስካላሟላ ድረስ ወደ ለንደን እንዳይገባ ባለፈው ዓመት የእንግሊዝ መንግስት እገዳ መጣሉ ይታወሳል። ይህም በመሆኑ ...

Read More »

የወጣት ሙጂብ አሚኖ የምስክርነት የድምጽ ፋይል ጠፋ በሚል ምክንያት የፍርድ ብያኔ ተራዘመ::

ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ በእስር ሲንገላታ በቆየው በወጣት ሙጂብ አሚኖ ክስ ጉዳይ ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2009 ዓ.ም ያስቻለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ችሎት፤ የመከላከያ ምስክሮች ላይብይን ለመስጠት የተሰጠውን የጊዜ ቀጠሮ አራዘመ። ወጣት ሙጂቦ ፣በእነ ኤሊያስ ከድር የክስ መዝገብ በሃሰት አልመሰክርም በማለቱ፣ እንዲሁም በእነ ከድር መሃመድ የክስ መዝገብ የተከሠሱትን እነ አቡበከር ...

Read More »