የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የነጻነት በአል አይከበርም አሉ

  (ኢሳት ዜና – ሀምሌ 3/2009) ደቡብ ሱዳን ስድስተኛውን የነጻነት ቀንን በፌሽታና በፈንጠዝያ እንደማታከብር የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር አስታወቁ።   ሳልቫኪር እንዳሉት ሀገሪቱ ከገጠማት ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ጋር በተያያዘ በአሉን በአደባባይ ከፍተኛ ወጭ አውጥታ ላለማክበር ወስናልች።   እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ የተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት በሀገሪቱ እየተባባሰ ለመጣው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ተደርጎ ተቀምጧል።   ከዚህ ጋር በተተያያዘም ይላሉ ሳልቫኪር የሀገሪቱ ዜጎችን ...

Read More »

በምስራቅ ኣፍሪካ 27 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልፈዋል ተባለ

  (ኢሳት ዜና – ሀምሌ 3/20009) የተባበሩት መንግስታት የሰብኣዊ መብት ድርጅት በምስራቅ ኣፍሪካ ከተከሰተው ከባድ ድርቅ ጋር ተያይዞ 27 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ኣስታውቀ።   እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በኣፍሪካ ቀንድ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ስደተኛ ዚጎች ቁጥር ከ4 ሚሊየን በላይ ኣሻቅቧል።   ከምስራቅ ኣፍሪካ ብቻ ባለፉት ስምንት ወራት 3 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጝች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሪፖርቱ ...

Read More »

ቴዎድሮስ ካሳሁን ኮንሰርት ለማዘጋጀት የመንግስትን ፈቃድ እየጠበቀ ነው

( ኢሳት ዜና – ሃምሌ 3 , 2009 )  ታውቂው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን በሚሊንየም አዳራሽ በአዲስ አመት ኮንሰርት ለማሳየት ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ፈቃድ ማስታውቂያ ክፍል ጥያቄ ቢያቀርብም ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግረን ምላሽ እንሰጥሃለን መባሉ ተዘገበ ። ቴዎድሮስ ካሳሁን ጷጉሜ 5 , 2009 አ.ም ለአዲስ አመት ዋዜማ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ ውል መዋዋሉን የድምጻዊው ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ገልጸዋል ። ኮንሰርቱን ...

Read More »

በአማራ ክልል ትጥቅ የማስፈታቱ ሙከራ አሁንም አልተሳካም

( ኢሳት ዜና -ሃምሌ 3 , 2009 ) በአማራ ክልል አርሶ አደሩን ትጥቅ ለማስፈታት ከሚሊሻ ሃላፊዎችና ከፖሊስ ጋር በተቀናጀ መልኩ የተጀመረው ዘመቻ ቢጠናከርም አሁንም አለመሳሳቱ ተነገረ ። በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ / ህውሃት / የሚመራው ወታደራዊ እዝ / ኮማንድ ፖስት / በመሳሪያ ምዝገባና በግብር ስም የጠራው ስብሰባ መጨናገፉም ተገልጿል ። በጎጃምና በጎንደር ድንገተኛ የቤት ለቤት ፍተሻ እየተካሄደ መሆኑንም የኢሳት ምንጮች ...

Read More »

የአማራና ኦሮምያ ክለብ ደጋፊዎች ህውሃትን ኣወገዙ

(ኢሳት ዜና – ሃምሌ 3 , 2009 )   የኦሮምያና የአማራ እግር ኳስ ክለቦች ደጋፊዎች በባህርዳር ስታዲየም የጋራ ትብብር ባማሳየት የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ ህውሃት / አገዛዝን አወገዙ ። የባህርዳር ከተማ ክለብና የኦሮምያ ለገጣፎ እንዲሁም የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት / አውስኮድ / ከሱሉልታ ጋር ሲጫወቱ የየክለቦቹ ደጋፊዎች በወዳጅነት መንፈስ በጋራ ሲጨፍሩ ታይተዋል:: በውድድሩ በባህርዳር ከተማና ለገጣፎ ተጫውተው 0 ለ ...

Read More »

ህዝባዊ አመጹ ሊደገም ይችላል የሚል ስጋት አለ

ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር እና ጎንደር ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴው ይጀመራል የሚል ስጋት መኖሩን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች በሸማቾች ተጣበው ታይተዋል። ዘጋቢያችን ከስፍራው በላከው መረጃ በቅርብ ቀናት አገዛዙ በወልቃይት ዙሪያ ለአመታት ምላሽ ሳይሰጥ የንፁሐንን ደም አፈስሶ በዜጎች ቤት ሀዘን ካስቀመጠ አመታት ሊደፍን ወራት በቀሩት በዚህ ጊዜ፣ አገዛዙ ላይ አጣነው ባሉት ...

Read More »

በትግራይ ድንበር የሚገኙ አርሶ አደሮች የባቡር መሬት ካሳ ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ፡፡

ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጅቡቲ ወደ መቀሌ በሚዘረጋው የባቡር መስመር እርሻ ቦታቸውን የተነጠቁ አርሶ አደሮች “ተገቢውን የመሬት ካሳ እንከፍላችኋለን” ቢባሉም ለሶስት አመታት ምንም ዓይነት የካሳ ክፍያ ባለማግኘታቸው ከነቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ገለጹ፡፡ በአማራ ክልል ቆቦ አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች በተለይ ለሪፖርተራችን እንደገለጹት፤ከመቀሌ እስከ ትግራይ ድንበር ድረስ ለሚገኘው አካባቢ ደረቅ መሬት በማለት የመሬት ካሳ ...

Read More »

የወልድያ ህዝብ የእለት ገቢ የግብር ተመንን ተቃወመ

ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወልድያ ትናንት የእለት ገቢን ምክንያት አድርጎ የተጣለውን ግብር ለመቃወም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በወልድያ የስብሰባ አዳራሽ የተገኘ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይም ተቃውሞውን በከፍተኛ ስሜት አቅርቧል። ወኪላችን እንደገለጸው ህዝቡ ስብሰባ እንዳለ በማወቁ በብዛት የወጣ ሲሆን፣ አዳራሽ በመሙላቱ ስብሰባውን በውጭ ሆኖ እስከ መከታተል ደርሷል። ህዝቡ “ እኛን ገድላችሁ፣ ማንን ልትገዙ ነው? ዜጎችን ...

Read More »

በኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት ማስከበር ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች 95 ከመቶ በላይ የሚሆኑት መዘጋታቸውን ጥናቶች አመለከቱ

ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገር አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መብት እና የዴሞክርሲ ግንባታ ላይ ለመስራት ፍቃድ ተሰጥቷቸው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ከመቶ በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በአሁኑ ወቅት አምስቱ ብቻ ስራቸውን እየሰሩ መሆኑን ቪዥን ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲ ጉባኤ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ጥናቶች አመለከቱ። ድርጅቶቹ እስከ ምርጫ 1997 ዓ.ም መባቻ ድረስ ስራቸውን በአግባቡ ያከናወኑ እንደነበርም ጥናቱ አመላክቷል። ...

Read More »

የኢትዮጵያ ፓርላማ ከ320 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

(ኢሳት ዜና – ሰኔ 30 2009) የኢትዮጵያ ፓርላማ 1/3ኛ የበጀት ጉድልት ያልበትን ከ320 ቢሊዮን ብር በላይ አመታዊ በጀት አጸ። የ100 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ያለበት የመንግስት አመታዊ በጀት ከብድር እና እርዳታ ይሸፈናል ጠብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል ። ዋናው ገቢ ግን ከግብር እና ከሃገር ውስጥ የሚሰበሰብ ነው ተብሏል። ይህ በጀት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ 17 በመቶ ብልጫ ያለው ቢሆንም የበጀት ጉድለቱ ...

Read More »