የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባት (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2009) የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባት (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 በጋራ ለመስራት ተስማሙ። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች በጋራ ለመታገልና ከሌሎች የኢትዮጵያ የለውጥ ሃይላት ጋር ለመተባበር መስማማታቸውን ድርጅቶቹ ጀርመን ፍራንክፈርት ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።  የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) እና አርበኞች ግንቦት 7 እኤአ ከሜይ 15 እስከ ሜይ 17 በጀርመን ፍራንክፈርት ለሶስት ...

Read More »

ዶ/ር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ የአውሮፓ ህብረት ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2009) የአውሮፓ ህብረት በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና የተመሰረተባቸው ክስ ውድቅ ተደርጎ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ጥሪ ቀረበ። በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሪፖርትን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው የአውሮፓ ፓርላማ በሃገሪቱና በኦሮሚያ ክልል ከተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግድያ በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲካሄድበት አሳስቧል። በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከወራት በፊት በህብረቱ ...

Read More »

በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ምክንያት የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ምትክ ቦታ አላገኙም ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2009) በአማራ ክልል ለጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ከቀያቸው የተፈናቀሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ለአመታት ምትክ ቦታ አለማግኘታቸው ተገለጸ። ለፋብሪካው ግንባታ ተብሎ ከመኖሪያ ይዞታቸው እንዲፈናቀሉ ከተደረጉት 213 አርሶ አደሮች መካከል 11 ዱ ብቻ ምትክ ቦታ እንደተሰጣቸው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘግበዋል። የስኳር ፋብሪካው ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በበኩሉ በፕሮጄክቱ ምክንያት ተፈናቅለው ካሳ ይገባቸዋል ከተባሉ ሁሉ ...

Read More »

ግብፅ ሱዳንና ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ በባለሙያዎች ደረጃ ሲያካሄዱ የነበረው ውይይት ባለመግባባት ተበተነ

ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2009) ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን ለ14ኛ ጊዜ በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ በባለሙያዎች ደረጃ ሲያካሄዱ የነበረው ውይይት ባለመግባባት ተበተነ። የሶስቱ ሃገራት ተወካዮች ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ ዙሪያ በአዲስ አበባ በመሰባሰብ የሁለት ቀን ምክክር ቢያደርጉም፣ 14ኛ ዙር ውይይት ያለውጤት መጠናቀቁን የግብፅ ባለስልጣናት ይፋ ማደረጋቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር የተሰኘ ጋዜጣ ሃሙስ ዘግቧል። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 እና ኦብነግ በጋራ ለመታገል ተስማሙ

ግንቦት ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄና የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት9 ቀን 2009 ዓም በፍራንክፈርት ከተማ፣ በሁለቱም ድርጅቶች ተወካዮች አማካኝነት ባደረጉት ስብሰባ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝና የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃና ስቃይ እንዲያበቃ በጋራ ለመታገል፣ ሌሎች ዲሞክራሲ ሃይሎችን በማሳተፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ሃይል እንዲያገኝ በግንባር ቀደምትነት ለመታገል ...

Read More »

በዶ/ር ቴዶዎድሮስ አድሃኖም ላይ የሚቀርበው ተቃውሞ ጨምሯል

ግንቦት ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ውስጥ በጤና ጥበቃ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ገዢው ፓርቲ፣ ታላላቅ አለማቀፍ ሃብታሞች የሚያፈሱትን የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረትን እርዳታ በመተማመን የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ለመመረጥ ከፍተኛ ዘመቻ እያካሄዱ ሲሆን ፣ በተቃራኒው ደግሞ በአገዛዙ ከፍተኛ በደል የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን የግለሰቡን መመረጥ አጥብቀው በመቃወም ...

Read More »

ኢሳት ወደ አየር ተመለሰ

ግንቦት ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለአንድ ሳምንት ያክል የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ኢሳት ከአየር ላይ እንዲወርድ ለማድረግ የቻለ ቢሆንም፣ አስተዳዳሩ ባደረው ከፍተኛ ጥርት ወደ አየር ለመመለስ ችሎአል። ሰሞኑን ሲደረግ የነበረው ሙከራ በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት ኢሳት ሙሉ በሙሉ የ24 ሰአት አገልግሎቱን ጀምሯል። ከ8 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ በሚፈልጉበት በዚህ ...

Read More »

በዮናታን ተስፋዬ ላይ የተላለፈው የጥፋተኝነት ብይን “አሳፋሪና በኢትዮጵያ የፍትህ መቀበርን” የሚያሳይ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተቃውሞ አቀረበ

ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ማክሰኞ በቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ላይ ያስተላለፈውን የጥፋተኝነት ብይን “አሳፋሪና በኢትዮጵያ የፍትህ መቀበርን” የሚያሳይ ዕርምጃ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተቃውሞ አቀረበ። መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሃገሪቱ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የሽብርተኛ ወንጀል ህግ በመንግስት ላይ ትችት የሚያቀርቡ ሰዎች የሚደርስባቸውን በደል ማሳያ መሆኑንም በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደረሃብ ሊለወጥ ይችላል ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል እየተባባሰ ያለው የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ሊለወጥ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። ካለፈው ወር ጀምሮ በክልሉ መጣል የነበረበት የበልግ ዝናብ በአብዛኛው ባለመጣሉ ምክንያት በአካባቢው ጉዳትን እያደረሰ ያለው የድርቅ አደጋ በመባባስ ላይ መሆኑን በድርጅቱ ስር የሚገኘው የረሃብ ቅድመ ትንበያ መምሪያ ገልጿል። ይኸው የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ለመድረስ አንድ ደረጃ ብቻ ወደሚቀረው ደረጃ አራት ...

Read More »

70 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት እንደማያገኙ ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ካላት አጠቃላይ ህዝብ መካከል እስከ 70 ሚሊዮን አካባቢ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት እንደማያገኝ የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።  በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን ለማስፋፋት መንግስት እየመደበ ያለው አንድ ቢሊዮን ብር አካባቢ በጀት እቅዱን ለማሳካት እንዳላስቻለው የሚኒስቴሩን የ10 ወራት ሪፖርት ለፓርላማ ያቀረቡት ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ መግለጻቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። “ከ60 እስከ 70 ሚሊዮን ህዝብ በገጠር በጨለማ ...

Read More »