ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ጥፋተኛ ተባለ

ግንቦት ፲፮ ( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከታህሳስ 15/2008 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘው የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ግንቦት16 ቀን 2009 ዓም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን፣ የቅጣት ውሳኔውን ግንቦት18፣ 2009 ዓም እንደሚሰማ ተነግሮታል። ፍርድ ቤቱ ፣ ጋዜጠኛው ከተለያዩ የሰማያዊ አባላት መረጃ በመሰብሰብ ኢሳት ለተሰኘ የቴሌቭዥን ጣቢያና ለግንቦት7 አመራሮች ማስተላለፉን ጠቅሷል። ...

Read More »

መምህር የሰው ወንድሙ ከአራት ወራት እስር በኋዋላ በነጻ ተለቀቀ

ግንቦት ፲፮ ( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ቤት የሕክምና መምህር ፣ የተቋሙ ዲን እንዲሁም ተመራማሪ የሆነው ወጣት የሰው ወንድሙ ማሙዬ ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት ሲሰቃይ ቆይቶ በነጻ ተለቋል። የሰው ወንድሙን የታሰረው “ አንድ ተጠርጣሪ የሆነ ግለሰብን መኖሪያ ቤትህ ለአንድ ቀን አሳድርሃል፣ እንዲሁም ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አለህ” የሚሉ መረተቢስ ውንጀላቸው ቀርበውበት ...

Read More »

ሱዳን የግብጽን ተሽከርካሪዎችና ታንከሮች መማረኳን አስታወቀች

ግንቦት ፲፮ ( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በዳርፉር አካባቢ ሰሞኑን በተደረገው ጦርነት የሱዳን ጦር ሃይል የግብጽን ተሽከርካሪዎችና ታንከሮች ከአማጽያኑ እጅ ላይ መማረኩን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት አልበሽር “ በዙሪያችን ያሉ አገራት እየፈራረሱ ነው፣ ጦራቸውም እየፈራረሰ ነው፣ ነገር ግን የሱዳን መከላከያ ሰራዊት የቱንም ያክል ሴራ እና ተንኮል ይሸረብበት፣ አሁንም በጥንካሬ ዘልቋል።” ብለዋል። የሱዳን ጦር ...

Read More »

በሳውዲ የሚኖሩ ከ700ሺ በላይ  የስራ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን አደጋ እንደተጋረጠባቸው የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ

ኢሳት ( ግንቦት 16 ፥ 2009) የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ የስራ ፈቃድ የሌላቸው ሰዎች ከሃገሪቱ እንዲወጡ ባስተላለፈው አዲስ መመሪያ ከ700 ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን አደጋ እንደተጋረጠባቸው የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ። ሃገሪቱ ያስቀመጠችው የ90 ቀናት የምህረት ቀን በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ የሚጠናቀቅ ቢሆንም፣ እስካለፈው ሳምንት ድረስ 8 ሺ 400 ኢትዮጵያውያን ብቻ ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ መቻላቸውን ለመረዳት ተችሏል። ከሳውዲ አረቢያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተከሰተው የምግብ ዕጥረት በቅርቡ ወደ ሰብዓዊ ቀውስ ሊለወጥ ይችላል ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 16 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተከሰተው የምግብ ዕጥረት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ሰብዓዊ ቀውስ ሊለወጥ እንደሚችል መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገው የቅድመ ረሃብ ማስጠንቀቂያ ተቋም ረቡዕ አሳሰበ። በአሁኑ ወቅት 7.7 ሚሊዮን የደረሰው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ተረጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም አለም አቀፍ ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው አዲስ ሪፖርት መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ...

Read More »

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በተመሰረበት የወንጀለኛ ክስ የጥፋተኝነት ብይን ተላለፈበት

ኢሳት (ግንቦት 16 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእስር ላይ በሚገኘው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ በተመሰረበት የወንጀለኛ ክስ ረቡዕ የጥፋተኝነት ብይን አስተላለፈ።  የነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ጌታቸው በመጀመሪያ ዙር የሽብተኛ ወንጀል ክስ ተመስርቶ የቆየ ቢሆን፣ ከሳሽ አቃቤ ህግ ክሱን ወደ መደበኛ ወንጀል ክስ ዝቅ ማደረጉ ታውቋል። ከሳሽ አቃቤ ህግ ጋዜጠኛው በአሜሪካ ሃገር የሚገኘው ጋዜጠኛ አበባ ገላው ከአምስት ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ የተላለፈውን ብይን የፍትህ እጦትን የሚያሳይ ድርጊት ነው አለ

የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ረቡዕ በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ላይ ያስተላለፈው የጥፋተኝነት ብይን በኢትዮጵያ ፍትህ እጦትን የሚያሳይ ድርጊት ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። “ጋዜጠኛው ከህዝብ በገሃድ የሚያውቀውን መረጃ ከመግለጽ ውጭ ያደረገው ነገር የለም” ሲሉ በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የምስራቅና የአፍሪካ ቀንድ ተወካይ የሆኑት ሙቶኒ ዋንዬኬ ገልጸዋል። ፍርድ ቤቱ በጋዜጠኛው ላይ የሚያስተላልፈው ፍርድም ተቀባይነት የሌለውና ጭካኔ የተሞላበት ነው በማለት ሃላፊው ተናግረዋል። “መንግስት ...

Read More »

ዶ/ር ቴዎድሮስ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመረጡ

ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች እጃቸው አለበት የሚባሉት እና በገዢው የህወሃት የአመራር ስልጣን ከፍተኛ ሃላፊነት ያላቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመረጡ። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩ ጊዜ የኮሌራ በሽታ እንዲደበቅ አድርገዋል በሚል በኒውዮርክ ታይምስና በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጦች ዘገባዎች ሲቀርቡባቸው እንደነበር ይታወሳል። የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለመሆን ...

Read More »

በሶማሌ ክልል ከ700 የሚበልጡ ሰዎች በአጣዳፊ ተቅማትና ትውከት በሽታ ህይወታቸው ማለፉን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ከ700 የሚበልጡ ሰዎች በአጣዳፊ ተቅማትና ትውከት በሽታ ህይወታቸው ማለፉን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። መንግስት በሽታው ኮሌራ አይደለም ቢልም የአለም ጤና ባለሙያዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታው ኮሌራ ስለመሆኑ የላቦራቶሪ ውጤት መገኘቱን እንዳረጋገጡ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይሁንና የአለም ጤና ድርጅት የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ክስተት ሲል በገለጸው ወረርሽኝ ባለፉት አራት ...

Read More »

በጋምቤላ የወባ በሽታ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መታመማቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ

ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2009) በጋምቤላ ክልል በማጃንግ ዞን ስር በሚገኙ አራት ቀበሌዎች የወባ በሽታ ወረርሽኝ መቀስቀሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ። በማጃንግ ዞን በመንገሺ ወረዳ በመሰራጨት ላይ ባለው በዚሁ ወረርሽኝ እስከአሁን ድረስ ከ550 የሚበልጡ ሰዎች ለህመም መዳረጋቸውንና በሽታው ወደ አጎራባች ቀበሌዎች ይዛመታል የሚል ስጋት ማሳደሩን ድርጅቱ በክልሉ ያለውን የበሽታውን ስርጭት አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርቱ አመልክቷል። በእስካሁኑ የበሽታው ስርጭት የሞተ ሰው ...

Read More »