ኢፈርት ተጠሪነቱ ለትግራይ ክልል ምክር ቤት እንዲሆን ተወሰነ

 (ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 17/2011)ግዙፍ ፋብሪካዎችንና የንግድ ተቋማትን የሚያስተዳድረው የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (ኢፈርት) ተጠሪነቱ ለትግራይ ክልል ምክር ቤት እንዲሆን ተወሰነ። ኢፈርት በሚል አህፅሮት የሚታወቀው በትግራይና የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚንቀሳቀሰው የሕወሃት ድርጅት ንብረት ተጠሪነቱ ወደ ትግራይ ክልል ምክር ቤት እንዲተላለፍ የተደረገው በህዝብ ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ነው ተብሏል። ኢፈርትን በተመለከተ በተለይም  በድርጅቱ ተጠሪነት ጉዳይ እና የፋይናንስ ግልፅነት ላይ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል። የሕዝባዊ ወያነ ...

Read More »

የሃገሪቱ የመጠባበቂያ እህል ክምችት መመናመኑ ተገለጸ

 (ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 17/2011)በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የእለት ደራሽ ድጋፍ ፈላጊዎች በመበራከታቸው የሀገሪቱ የመጠባበቂያ እህል ክምችት መመናመኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ። ይህንንም ተከትሎ 6 ሚሊዮን ኩንታል እህል ከውጭ ለማስመጣት ጨረታ መውጣቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ከመጠባበቂያ እህል ክምችት በማውጣት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች እርዳታና ድጋፍ ማድረግ የተለመደ ነው ። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚከሰቱ ...

Read More »

በጌድዮ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 17/2011)በጌድዮ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን በአካባቢው የተሰማሩት የህክምና ባለሙያዎች ገለጹ። በየወገኖቻቸውንና በተለያዩ አካባቢዎች የነበሩት ተፈናቃዮች እርዳታ ለማግኘት ወደ አካባቢው በመምጣታቸው ቁጥሩ ሊጨምር መቻሉንም ገልጸዋል። ለተፈናቃዮቹ የተለያዩ እርዳታዎች እየተደረጉ ቢሆንም ከቁጥራቸው ብዛት አንጻር ግን ለሁሉም ማዳረስ አስቸጋሪ መሆኑን ነው የተናገሩት። ተፈናቃዮቹ ክረምቱ ከመግባቱ በፊት ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ ማድረግ ቢቻል ከክረምቱ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን አደጋ ለመቀነስ ይችላል ብለዋል። በጌዲዮ ...

Read More »

በባሌ ዞን ሮቤና በጎባ ከተማ እየተበተኑ ያሉ የዛቻ ወረቀቶች በነዋሪው ላይ ስጋት መደቀናቸው ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 17/2011) በባሌ ዞን ሮቤና በጎባ ከተማ እየተበተኑ ያሉ የዛቻ ወረቀቶች በነዋሪው ላይ ስጋት መፍጠራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። በጽሁፉ ላይ መጤዎችን በማስወጣት የኦሮሞ ህዝብ ነጻነቱን በአካባቢው ላይ ለማስፈን ይሰራል የሚል እንደሚገኝበት የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የማስጠንቀቂያ ጽሁፍን የሚበትነው አባቶርቤ የተባለ ቡድን መሆኑንም የአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጠዋል። በባሌ ዞን ሮቤና በጎባ ከተማ እየተበተኑ ያሉት የማስፈራሪያ ወረቀቶች ራሱን አባ ቶርቤ ብሎ ከሚጠራው ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ነች ሲሉ ተናገሩ

 (ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 17/2011) አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነች ሲሉ የኦዲፒ ሊቀ መንበር እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ። የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ) 29ኛ የምስረታ በዓል በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት  ሲካሄድ ዶክተር አብይ እንደገለጹት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባህር ዳር፣ መቀሌ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምት ሄዶ እንደሚሰራውና የኔ ናቸው እንደሚለው ሁሉ አዲስ አበባም የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ መሆኗን ማወቅ ያስፈለጋል። በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ...

Read More »

በፕሬዝዳንት ትራምፕና በሩሲያ መካከል ድብቅ ሴራ ስለመኖሩ መረጃ አለማገኘቱ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011) በፕሬዚዳንት ትራምፕና በሩሲያ መካከል ድብቅ ሴራ ስለመኖሩ መረጃ አለማግኘቱን ጉዳዩን ለማጣራት የተቋቋመው ልዩ ምክር ቤት አስታወቀ። በሮበርት ሙለር የሚመራው ልዩ ምክር ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ላለፉት ሁለት አመታት ሲያደርግ የቆየውን ማጣራት በተመለከተ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዊሊያም ባርም የልዩ ምክር ቤቱን የሁለት አመት የምርመራ ውጤት ለኮንግረሱ አቅርበዋል። በሮበርት ሙለር የተመራው ልዩ ምክር ቤት የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ...

Read More »

የአማራ ክልል ለተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያሰባስበው ኮሚቴ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ብር አለቀበልም አለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011)በአማራ ክልል ለተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያሰባስበው ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠውን 4.7 ሚሊዮን ብር አልቀበልም አለ። በክልሉ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያሰባስበው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር በሰጡት መግለጫ “ለአማራ ሕዝብ የገባው ቃል ከባንኩ የምንጠብቀው ባለመሆኑ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃል የገባውን ገንዘብ አይቀበልም” ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች 100 ሚሊዮን ብር መለገሱን አስታውቆ ነበር። ...

Read More »

የአርበኞች ግንቦት 7 ስብሰባ በገጠመው ተቃውሞ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተራዘመ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011)የአርበኞች ግንቦት 7 የባሕር ዳር ውይይት በከተማዋ በተፈጠረ ረብሻ ለሌላ ጊዜ ተራዘመ፡፡ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በባሕር ዳር ከተማ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጠራው ሕዝባዊ ውይይት ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማህኝ አስረስ ሰብሰባውን በሀይል ለማደናቀፍ መሞከሩ ዲሞክራሲን ወደኋላ የሚመልስ ነው ብለዋል። የአርበኞች ...

Read More »

አዴፓ በስግብግብነት የታሪክ እና የስልጣን ሽሚያ ውስጥ እንደማይገባ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 16/2011)የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ በስግብግብነት የታሪክ እና የስልጣን ቦታ ሽሚያ ውስጥ አይገባም ሲሉ የፓርቲው የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ገለጹ አዴፓ በፓርቲው የሁለት ቀናት የማዕከላዊ ኮሚቴ  ስብሰባ የውይይት ጭብጦችና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ዶክተር አምባቸው መኮንንን የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ ዘጠኝ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚዎችንም ለይቷል። የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ በባህርዳር ከተማ ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የባለ አደራ ኮሚቴ በሚል የሚስተዋለው እንቅስቃሴ  ሕገ ወጥ ነው አሉ

 (ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አዲስ አበባን በተመለከተ የባለ አደራ ኮሚቴ በሚል የሚስተዋለው እንቅስቃሴ  ሕገ ወጥ ነው ሲሉ አስጠነቀቁ። ዶክተር አብይ  አህመድ የፖለቲካ በሽታና ችግር በልሂቃን፣ በአክቲቪስቶች እና በፖለተከኞች ላይ የሚስተዋል ችግር መሆኑንም አዲስ ወግ በተሰኘው የውይይት መድረክ  ላይ ባደረጉት ንግግር  አንስተዋል። በኢትዮጵያ በምርጫ በሚካሄድ ፉክክር ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ፈቃደኝነታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በባላደራ ስም በሚደርግ አይነት ...

Read More »