ከፍተኛ ወጪ የወጣበት የዲያስፖራ ቀን ለማክበር እንቅስቃሴ ተጀምሯል

ሰኔ ፩ ( አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን ከሃረር እንደዘገበው የዲያስፖራውን ቀን ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 24 የሚቆይ የዲያስፖራ ቀን በሃረር ለማክበር ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ዝግጅት እየተደረገ ነው። ወኪላችን እንደሚለው በአካባቢው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ባለበት እንዲሁም ድርቅ በገባበት ወቅት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ በአል ማክበር አሳዛኝ ነው። የዲያስፖራ አባላትን በቤትና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በመደለል ወደ አገር ውስጥ ...

Read More »

የኬኒያ ፖሊስ 40 ህገወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን አስታወቀ

ሰኔ ፩ ( አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ረቡእ ምሽት ላይ በማና ክፍለሃገር ኬዮሌ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል። በአንድ ትንሽ ቤት ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ ተቀምጠው እያሉ መያዛቸውንና እድሜያቸው ከ10 እስከ 25 ዓመት የሚሞላቸው ታዳጊዎችና ወጣቶች መሆናቸውንም ፖሊስ አስታውቋል። ከመሃከላቸው የእንግሊዝኛም ሆነ የስዋሂሊ ቋንቋ ተናጋሪ የለም። እንዴት ወደ ኬንያ እንደገቡ ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑንም የአገሪቱ ...

Read More »

በአወዳይ አምስት ሰዎችን የገደለው ግለሰብ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገደለ

ግንቦት ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በአወዳይ ከተማ 5 ሰዎችን በሽጉጥ ተኮሱ የገደለው አቶ አብዲ እድሪስ የተባለው የቀበሌ አስተዳዳሪ ማታ ከምሽቱ 3 ሰአት ላይ ከመስጊድ ሲወጣ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድሏል። ወኪላችን እንደገለጸው በርካታ ጥይቶ ያረፉበት ግለሰቡ፣ ሰውነቱ በጥይት ተበሳስቷል ብሎአል። ባለስልጣኑ ድርጊቱን ከፈጸመ በሁዋላ ለጥቂት ጊዜ ታስሮ የተፈታ ሲሆን፣ ፍርድ ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ሚሊሺያዎች ስልጠና እየወሰዱ ነው

ግንቦት ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በሶማሊያና በኦሮሚያ ድንበሮች አካባቢ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የኦሮምያ ክልል በርካታ ልዩ ሚሊሺያዎችን ማሰልጠን መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል። የሚሊሺዎቹ ስልጠና በሶማሌ ክልል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ነው ሲሉ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቤቱታ አቅርበዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ከእያንዳንዱ የኦሮሚያ ወረዳ 8 አጠቃላይ ከ362 የኦሮሚያ ወረዳዎች 2896 የሚሆኑ እድሜያቸው ከ18 እስከ 30 የሚሆኑ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ብቻ ከ12 ሺ በላይ እናቶች ህጻናትን ይዘው በልመና ህይወታቸውን ይገፋሉ ተባለ።

ግንቦት ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ሀገር አቀፍ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የምክክር መድረከ ላይ የቀረበ ጥናት እንደሚያሳያው በአዲስ አበባ ቤተሰብ አልባ ለችግር የተጋለጡ ህፃናትን ይዘው የሚለምኑ እናቶች ቁጥር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። አብዛኞቹ እናቶች ከተለያዩ የአማራ ክልል ወረዳዎች የመጡ ናቸው። አጥኝዎች እንደሚሉት በገጠር እየከፋ የመጣው ድህነት ፥ እናቶች ራሳቸውን ለማስተዳደር የሚችሉበትን ...

Read More »

በመቀሌ እና ባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ መካከል የተከሰተውን አለመግባባት ተከትሎ ውዝግቡ ተካሯል፡፡

ግንቦት ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል እግር ኳስ ፊዴሬሽን የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፊድሬሽን ያስተላለፈውን ውሳኔ አውግዟል፡፡ ውሳኔው ህግና ስርዓቱን ያልተከተለና ለመቀሌ ያደላ ነው ያለው የአማራ ክልል እግር ኳስ ፊዴሬሽን ፥ ፊዴሬሽኑ ያሳለፈው ውሳኔ በተፅኖ ነው ሲል ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ የጣናው ሞገድ የባህር ዳር ከነማ ስራ አሰፈፃሚዎች በበኩላቸው ከዚህ በኃላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብለን ...

Read More »

በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት በየዓመቱ እየተባባሰ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ

ግንቦት ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤጀንሲ ጽህፈት ቤት ይዞ በወጣው የወርሃዊ የዋጋ ዝርዝር ጥናት መሰረት በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በምግብ ነክና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪዎች መታየታቸውን አስታውቋል። ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ 12 ነጥብ 2 ከመቶ የነበረው የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ወደ 12 ነጥብ 3 ከመቶ ከፍ ብሏል። ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች በበኩላቸው ...

Read More »

ኢትዮጵያና ግብፅ የአባይ ግድብ ውሃ መሙላት በሚጀምርበት የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ድርድር እያካሄዱ መሆናቸው ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2009) የግብጽ ባለስልጣናት በመገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ ውሃ መሙላት በሚጀምርበት የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ገለጹ። የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከዚህ በፊት በሁለቱ ሃገራት መካከል ሲካሄድ በቆየ ድርድርና ስምምነት ወቅት ግድቡን በውሃ የመሙላቱ ሂደት እንዲዘገይ ጥያቄን ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። የግብፅ ባለስልጣናት ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ በጥናት ተደግፎ እስኪቀርብ ድረስ የግድቡ የግንባታ ...

Read More »

ሃሳባቸውን በተለያዩ መንገዶች የሚገልጹ ሰዎች የሚተላለፍባቸው የእስር ቅጣት እንዳሳሰበው ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ሃሳባቸውን በተለያዩ መንገዶች የሚገልጹ ሰዎች ለእስር መዳረግና የሚተላለፍባቸው የእስር ቅጣት እንዳሳሰበው ገለጸ። በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዳይጓዙ የተደረጉት የምክር ቤቱ ሃላፊ ዘይድ ራ’ድ አልሁሴን፣ ለመንግስት ገለልተኛ ምርመራ በሃገሪቱ ለማካሄድ ያቀረቡት ጥያቄ አሁንም ድረስ ምላሽ አለማግኘቱን አስታውቀዋል። ምክር ቤቱ በስዊዘርላንድ ጀኔቭ ከተማ እያካሄደ ባለው ጉባዔ ሪፖርትን ያቀረቡት ...

Read More »

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 8.7 በመቶ ማደጉን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ መጨመረን ተከትሎ የሃገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 8.7 በመቶ ማደጉን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ረቡዕ አስታወቀ። በግንቦት ወር የምግብ ነክ ሸቀጦችን ግሽበት 12.3 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፣ በሚያዚያ ወር ግሽበቱ 12.2 እንደነበር ሮይተርስ የኤጀንሲውን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጣሸቀጦች ግሽበት ባለፈው ወር ከነበረበት 4.6 በመቶ ወደ 4.7 በመቶ ከፍ ማለቱም ታውቋል። ...

Read More »