Author Archives: ESAT Amsterdam

በጋሞ ጎፋ ዞን ባለው ድርቅ ሰዎችና እንስሳት ህይወታቸው እያለፈ ነው

ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች፣ አርሶአደሮች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት ያለቁ ሲሆን፣ ሰዎችም መሞት ጀምረዋል። ድንችና የመሳሰሉት ሰብሎች በዝናብ እጥረት መጥፋታቸውን የሚገለጹት ነዋሪዎች፣ በሴፍትኔት እንዲታቀፉ ለተደረጉ ካድሬዎች እህል ቢከፋፈልም አብዛኛው ህዝብ እርዳታ ባለማግኘቱ ከፍተኛ አደጋ ተደቅኖበታል። በድርቁ በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቁት መካከል ኮንሶ፣ ደራሸ፣ ...

Read More »

ከዎላይታ ዞን ወደ ሲዳማ ዞን በኃይል ለማካለል የተጀመረውን እንቅስቃሴ የዎላይታ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ዎህዴግ/ ተቃወመ

ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዎህዴግ ሰኔ 3 ቀን 2009 ዓም ባወጣው ባለ 4 ገጽ መግለጫ የዎላይታ ህዝብ ብዛትና የመሬት ጥበትን ተከትሎ የዎላይታ ወጣቶች በትምህርት መቅሰሚያ ዕድሜኣቸው ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየሄዱ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮኣቸውን እየገፉ መሆኑን ጠቅሶ፣ በአካባቢው ያለው የመሬት ጥበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ጊዜ፣ አሁን ደግሞ ‹‹ ...

Read More »

የዋልድባ ገዳም መነኮሳት በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ተዘገበ

ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት ከእስር የተፈታው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣው ዘገባ እንደገለጸው መነኮሳቱ በጎንደር ከተማ በነበረው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተሳትፈዋል ተብለው ይፈለጉ ለነበሩ ግለሰቦች ከለላ ሰጥተዋል በሚል ምክንያት የሽብርተኝነት ክስ ተከፍቶባቸዋል፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት ሰኔ 20/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ...

Read More »

የትምህርት ሚኒስትሩን የዝርፊያ ሰንሰለት የሚያሳዩ ተጨማሪ መረጃዎች እየመጡ ነው

ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አሁን ትምህርት ሚኒስቴርን የሚመሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሙስና መዘፈቃቸውን በተመለከተ ኢሳት መረጃዎችን ማውጣቱን ተከትሎ፣ የክልሉ ነዋሪዎች በተለይ የአቶ ሽፈራውን የሙስና ሰንሰለት የሚያሳዩ መረጃዎችን እየላኩ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው የአቶ ሽፈራው የሙስና ሰንሰለት እስከ ወረዳ የተዘረጋ ነው ይላሉ። ...

Read More »

ወደ ማላዊ ሲገቡ የነበሩ 26 ኢትዮጵያዊያን መያዛቸውን የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ

ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ድንበር ቆራርጠው በማላዊ የድንበር ከተማ ካሮንጋ በኩል በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ተጭነው የነበሩ 26 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በድንበር ፖሊስ መያዛቸውን የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪዎችን ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪ ከቺቲፓ ወደ ካሮንጋ አውራጃ የሚወስደውን M1 አውራ ጎዳና ይዘው ሲጓዙ ነበር። የድንበር ፖሊሶችን መምጣት በማየት መንገዳቸውን ቀይረው በካሮንጋ አየር ...

Read More »

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና አቶ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት የሙስና ሰንሰለት ከፍተኛ ገንዘብ እየመዘበሩ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ

ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት ከፍተኛ የዝርፊያ ሰንሰለት በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መዝረፋቸውን ከአስተማማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የምንጮቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል፣ ምረመራውን ያካሄደውን የኦዲት ክፍል ለመግለጽ ባንችልም፣ መርምራውን የካሂዶት ኦዲተሮች ግማሾቹ ማስፈራሪያ ደርሶአቸው ስራቸውን ለቀዋል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ክልሉ ወንዶ ኢንዶውመንት ኩባንያዎች ...

Read More »

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኮማንደሮችን ስራ መልቀቅ በተመለከተ ለኢሳት ዘገባ መልስ ሰጠ

ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽኑ መልሱን የሰጠው ኢሳት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኪሚሽነር ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁና የምዕራብ ጎጃም ዞን የወንጀል ምርመራ ሃላፊ የነበሩት ኮማንደር በላይ ካሴ ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በማስመልከት ዘገባ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሽብር ማህበራዊ ሚዲያ አራማጆች የአማራ ክልል ኪሚሽን ስራ ባልደረባ የሆኑት ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁና ኮማንደር በላይ ...

Read More »

በማእከላዊ ዜጎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው

ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት ሸራተን እየተባለ በሚጠራው የእስር ቤቱ ክፍል የሚገኝ ዘርኣይ አዝመራው የሚባል ከደባርቅ አካባቢ የመጣ ወጣት አባትህ ሸፍቷል በሚል በአሌክትሪክ “ ሾክ” ስለተደረገ ሰውነቱ እንደሚንቀጠቅ፣ በራሱ መሄድ ባለመቻሉም በድጋፍ እንደሚጓዝ ታውቋል። ሌሎችም በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች ተይዘው የመጡ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ ድብደባ የተፈጸመባቸው በመሆኑ ለአካል ጉዳት ተደርገዋል። አእምሮን በሚጎዳ ...

Read More »

የኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ሠራተኞች በቻይናውያን አሠሪዎቻቸው ድብደባ ደረሰባቸው

ሰኔ ፲፱( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሀዋሳ የቻይናውያን ኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሠራተኞች በቻይናውያን አሰሪዎቻቸው የከፋ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው በተለይ ለኢሳት ገለጹ። የፕሮጀክቱ ሠራተኞች እንደገለጹት በአሰሪዎቻቸው የከፋ ድብደባ የተፈጸመባቸው ላለፉት ወራት ያልተከፈላቸውን ደመውዝ እንዲከፈላቸው በጋራ ጥያቄ በማቅረባቸው ነው። “የሠራንበት የላባችን ዋጋ ሊከፈለን ይገባል። የሠራንበትን ደመወዝ ባለማግኘታችን ቤተሰቦቻችን ችግር ላይ ወድቀዋል” በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም ...

Read More »

በምስራቅ ኢትዮጵያ በምግብ እጥረት የተጠቁ ሕጻናት አስር እጥፍ መጨመሩን እና 67 ሕጻናት በርሃብ መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ

ሰኔ ፲፱( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ በኦጋዴን ዶሎ ዞን ያለው የርሃብና ያልተመጣጠነ ምግብ እጥረት አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን በአካባቢው የተሰማራ የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ። ”ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ በዶሎ ዞን ነዋሪ የሆኑ ታዳጊ ሕጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋላጭ ሆነዋል። የሕክምና ቡድናችን ባለፉት አስር ዓመታት በአካባቢው የሥራ ቆይታችን እንደዚህ ዓይነት ዘግናኝ ...

Read More »