ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የዋስትና መብት ተከለከለ

የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሕግ አግባብ ውጪ የሸብር ክስ ተመስርቶበት በእስር ላይ የሚገኘው የነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው የዋስትና መብት ተከልክሏል። ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ያቀረበውን የዋስትና መብት ጥያቄ የተመለከተ ሲሆን፣ ”ተከሳሹ በዋስ ቢወጣ በሕጋዊም ሆነ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ስለሚችል የዋስትና ጥያቄውን አልተቀበልነውም” የሚል ውሳኔ ሰጥቷል።
ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ”ይግባኝ ባይ ቋሚ አድራሻ የለውም” በማለት ይግባኙ ውድቅ መደረጉን በምክንያትነት አቅርቧል። ተከሳሽ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው አስቀድሞ ቋሚ የመኖሪያ አድርሻውን በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠይቆ ማስመዝገቡ የሚታወቅ ሲሆን፣ የፍርድ ቤቱ ፍርደ ገምድል ውሳኔ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር ውሳኔው ፖለቲካዊ ብይን መሆኑን ነው ሲሉ ታዛቢዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።