ገዥው ፓርቲ በፈጠረው ጫና ላለፉት አስር ቀናት ተቋርጦ የነበረው የኢሳት ቴሌቪዥን ስርጪት ዳግም ተጀመረ።

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ሀሳቦችን እንዳይሰማ ካለው ሥጋት በመነሳት እንደተለመደው ሁሉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሠስ የኢሳት ቴሌቪዥን ከአየር ላይ እንዲወርድ አድርጎ ቢሰነብትም ኢሳት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ዳግም ወደ አየር ተመልሷል።
ቀደም ሲል ኢሳትን ሲከታትተሉ የነበሩ አድማጮች የዲሽ ሰሀን አቅጣጫ መቀየር ሳያስፈልጋቸው በፍሪኩዌንሲ Tel Star 12
Frequency 12738 Horizontal ,SR 5184 , FEC 2/3 እንደወትሮው ሁሉ የኢሳትን ፕሮግራሞች መከታተል ይችላሉ።
ከዚህም ባሻገሪሳት በናይል ሳት እያስተላለፈው ያለው የሬድዮ ስርጪት እንዳለ የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል።