የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ አዲስ ማእቀብ ለመጣል መወሰኑን ተከትሎ በሁለቱ አገሮች ውጥረቱ ጨመሯል

ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ አዲስ ማእቀብ ለመጣል መወሰኑን ተከትሎ  በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ውጥረት መጨመሩ ታወቀ

ደብረብርሀን ብሎግ  የጦር መሳሪያና ሰራዊት የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰሜን አዲስ አበባ በኩል ሲጓዙ እንደነበር ዘግቧል።

ኢሳት ወደ ሰሜን የአገሪቱ ክፍል በመደወል እንዳረጋገጠው ከሆነ እረቡ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የሚመሩ ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ በርካታ አውቶብሶች ወደ ሰሜን ተጉዘዋል።

በድንበር አካባቢ ያለውን ሁኔታ  ለማወቅ ባይቻልም፣ የጸጥታው ምክር ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ችግር ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊቀይረው ይችላል።

የመለስ መንግስት በቅርቡ የተወሰነ ሰራዊቱን ወደ ሶማሊያ፣ የተወሰነውን ደግሞ በሰላም አስከባሪ ስም ወደ ሱዳን መላኩ ይታወሳል።

የኤርትራ መንግስት በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መንግስት ግፊት የጸጥታው ምክር ቤት የወሰነውን ውሳኔ ተቃውሟል።

ይሁን እንጅ የማእቀቡ ጠንካራ አለመሆን የኢትዮጵያን መንግስት ማበሳጨቱም ይነገራል።