የጎንደር ማረሚያ ቤት ሃላፊ ታሰሩ

ኅዳር ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ካለፈው አርብ ጀምሮ በቁጥጥር ስር የሚገኙት ኢንስፔክተር ልጃለም መሰረት የታሰሩት ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ጋር በተያያዘ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ኢንስፔክተሩ ባለፈው አርብ ኮሎኔል ደመቀ ፍርድ ቤት ቀርበው በነበረበት ወቅት እጃቸው በካቴና ሳይታሰር እንዳይቀርቡ አድርገዋል በሚል ነው። ኢንስፔክተሩ እስካሁን ደረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።

የአካባቢው ፖሊሶች የኢንስፔክተሩን መታሰር አጥብቀው እየተቃወሙት ነው።