የደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሟቸውን ገለጹ

ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡዕ የብሄር ብሄረሰቦችን በአል ለማክበር በሚል በዩኒቨርስቲው በተጠራ ዝግጅት ላይ ተማሪዎች ጩትና ተቃውሞ እያሰሙ ከአዳራሹ ሲወጡ፣ መምህራን ደግሞ በቀረበው የመወያያ ጽሁፍ ላይ ምንም ሳይናገሩ በዝምታ ተቃውሞአቸውን በመግለጽ ዝግጅቱ ተዘግቷል።

ምሳ ሰአት አካባቢ ተማሪዎች ውሸት በቃን ፣ አጋዚ ግቢያችን አይግባ፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ይመስረት፣ መብታችን ይከበር በማለት ከ1 ሰአት በላይ ግቢያቸውን እየዞሩ አገዛዙን ሲቃወሙ መውለዋል።

የአጋዚ ወታደሮች ወደ ዩኒቨርስቲው በመግባት በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ ፈጽመዋል።