የእንግሊዝ መንግስት ለአንባገነን አገራት መሳሪያ መሸጡን እንዲያቆም ሲሉ የአገሪቱ ዜጎች ጠየቁ

መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእንግሊዝ መንግስት ዜጎቻቸውን ለሚጨቁኑ፣ሰብዓዊ መብቶችን ለሚጥሱ አንባገነን መንግስታት መሳሪያ መሸጡን እንዲያቆም ሲሉ ”የመሳሪያ ሽያጩ ፍትሃዊ ይሁን’ የሚል መፈክር ያነገቡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ተይንተ ሕዝብ አካሄደዋል።
ጸረ ጦርነት ባነሮችን የያዙት ሰልፈኞች የእንግሊዝ መንግስት አፋኝ ለሆኑት አገራት ኢትዮጵያ፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ባሕሬን እና ቬንዙዌላን ለመሳሳሉ አንባገነኖች መሳሪያ በመሸጥ ሰላማዊ ዜጎችን ከማስጨፍጨፍ ሚናውን እንዲታቀም ሲሉ ጠይቀዋል።
የሳኡዲ አረቢያ መንግስት በየመን ላይ የጦር የተከለከሉ ክላስተር ቦንቦችን በሰላማዊ ዜጎች ላይ መጠቀሙንምንም አውግዘዋል። ”ለምን የእንግሊዝ መንግስት ከ3 ሽህ 500 በላይ ሕጻናት ለገደለው የሳኡዲ አረቢያ መንግስት መሳሪያ ይሸጣል?” ሲሉ ድርጊቱን ኮንነዋል።
ከሳኡዲ አረቢያ በተጨማሪም ሜክሲኮ፣ ባህሬን፣ እስራኤል፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም ንጹህና ዜጎችን ይገላሉ ሲል ግሎባል ቮይስ ዘግቧል። እንግሊዝ ከአሜሪካ ቀጥላ ወታደራዊ መሳሪያዎችን በማምረት ለሽያጭ የምታቀርብ አገር መሆኗ ይታወሳል።