የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በሙስና የተዘፈቀ መሆኑ ተነገረ

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ወ/ሮ እሌኒ ገብረመድህን የሚመሩት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በሙስና የተዘፈቀ መሆኑ ተመለከተ

ወንዶሰን መዝለቂያ ከአለም ባንክ ያገኙዋቸውን መረጃዎች በማያያዝ ባወጡት የምርመራ ዘገባ የሸቀጦች ገበያ ድርጅት በሙስና መዘፈቁን የሚያሳዩ ግልጽ መረጃዎች ቢኖሩም፣ ሙስናን እዋጋለሁ የሚለው የጸረ ሙስና ኮሚሸንም ሆነ ጉዳዩን ጠንቅቀው የሚያዉቁት አቶ መለስ ዜናዊ ምንም እርምጃ አልወሰዱም።

የአለም ባንክ ወ/ሮ ኢሌኒ ለሚመሩት  ድርጅት ሰጥቶት የነበረውን 4 ሚሊየን 8 መቶ 55 ሺ 8 መቶ ዶላር ወይም 84 ሚሊዮን 102 ሺ 456 ብር ሙስና ተፈጽሞበታል በሚል ሰርዟል። ገንዘቡ የተሰጠው መንግስት የአለም ባንክ ከሰጠው ገንዘብ መካከል የተወሰነውን የድርጅቱን አቅም ለመገንባት እንዲያውለው በጠየቀው መሰረት ነበር።

የወ/ሮ ኢሌኒ ድርጅትም ጨረታ በማውጣት ጨረታውን  ሚሊኒየም አይቲ የተባለ በስሪላንካ የሚኖር ድርጅት ማሸነፉን አስታውቆ የኮንትራት ስምምነት ለመፈራራም በሚዘጋጅበት ወቅት ነበር፣ ጥቆማ የደረሰው የአለም ባንክ በጨረታው ሂደት ሙስና ተፈጽሞአል በሚል እንዲሰረዝ የተደረገው።

ባንኩ ያወጣው ሪፖርት ለቶ መለስ ዜናዊ የተላከላቸው ቢሆንም እርሳቸው ግን ምንም አይነት እርምጃ ሳይወስዱ ቀርተዋል።

በጨረታው ሂደት ላይ ሚሊኒየም አይቲ 3 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ዶላር ቢያቀርብም፣ ለአለም ባንክ ግን ድርጅቱ ለ4 ሚሊ ን 855 ሺ ዶላር እንዳቀረበና እንዳሸነፈ ተደርጎ ቀርቧል፤ በዚህም የወ/ሮ እሌኒ ድርጅት ስራተኞች ከ 1 ሚሊዮን 270 ሺ ዶላር ወይም ከ20 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ሊወስዱ ሲዘጋጁ የአለም ባንክ ባለስልጣናት ይዘዋቸዋል።

ጉዳዩ እንዲድበሰበስ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት ወ/ሮ እሌኒና ባልደረቦቻቸው ፣ ምሲጢሩ እንደታወቀ ጨረታውን ያለምንም ማንገራገር ሰርዘዋል።

የጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲህ አይነት በግልጽ የተፈጸመን ሙስና ለማጣራት ያልቻለው በሙስናው ዙሪያ የህወሀት ባለስልጣናትም በመሳተፍ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።  

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide