የኢህአዴግ ደጋፊዎች በእስራኤል አገር የሚገኙ አትዮጵያውያን ያካሄዱትን ስብሰባ ለማወክ ቢሞክሩም አልተሰካላቸውም ሲሉ አዘጋጆች ገለጡ

መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በእስራኤል አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሮች ዙሪያ ለመነጋገር፣  በእስራኤል አገር ስላለው የስደተኞች መብቶች ለመነጋጋር እንዲሁም በመገለላቸውና በዘረኝነት የተነሳ የመገለልና የባይተዋርነት ስሜት የሚሰማቸውን ቤተ እስራኤላውያንን ለመርዳት የተቋቋመው ማህበር ባለፈው አርብ ፣ እኤአ ኦክቶበር 5፣ 2012 በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ያደረገውን ስብሰባን  የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ለማሰናከል ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው በመቅረቱ በፖሊስ ተገደው አዳራሹን ጥለው ወጥተዋል።

የማህበሩ ሊቀመንበር የሆነው ወጣት ሳሙኤል አለባቸው ለኢሳት እንደገለጠው  ስብሰባው ለመጀመሪያ ጊዜ ገዢው ፓርቲ በእስራኤል ውስጥ የነበረውን የበላይነት ማጣቱን ያሳየ ነበር ብሎአል።

ወጣት ሳሙኤል የገዢው ፓርቲ ሰዎች ሃሳባቸውን እንደማንኛውም ሰው ቁጭ ብለው  ቢገልጹ ኖሮ ይመረጥ እንደነበር አስታውሶ ፣ ስበሰባው ከመጀመሩ በፊት  ችግሩን ለመፍታት ሙከራ አድርገው እንደነበር ተናግሯል

በእለቱ ስብሰባ ላይ አቡነመቃርዮስ እግዚአብሄር ገዢውን ፓርቲ ህዝቤን ልቀቅ እያለው መሆኑን ለተሰብሳቢው ተናግረዋል ቪዲዮ

የቤተእስራኤላዊያኑ የሀይማኖት መሪ የሆኑት ራብ ያፊቅ አለሙ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን አንድ ከሆኑ ነጻ መውጣት ይችላሉ ብለዋል።

አንዳንድ ተሳታፊዎች፣ መንግስት ጥሩ ነገሮችን ሲሰራ ለምን ጥሩ እንደሰራ አይገለጽለትም በማለት የስብሰባውን መሪ ጠይቀው መልስ ተሰጥቷቸዋል  ቪዲዮ ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide