የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በአዋጁ ዙሪያ ከነዋሪው ጋር ያደረጉት ውይይት ተቃውሞ ቀረበበት

ጥር 5 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-የከተማ ቦታን አስመልክቶ የወጣው አዲስ አዋጅ ፓርላማ በተባለው የኢህአዴግ አባላት ሸንጎ ከፀደቀ በሁዋላ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በአዋጁ ዙሪያ ከነዋሪው ጋር ያደረጉት ውይይት  ተቃውሞ ቀረበበት።

የአቶ ኩማ አስተዳድር ቢሊዝ አዋጁ ላይ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ በተለየ መልኩ የተስተጋባው ተቃውሞ፤ የራሱ የውይይት መድረኩn መዘጋጀቱ  ፋይዳነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው።

ምክንያት፦  የሊዝ አዋጁ ለውይይት ተብሎ ወደ ነዋሪው የወረደው፤ በፓርላማ ከፀደቀ በሁዋላ በመሆኑ እንዲሁም፤ ውይይቱን የመሩት ከንቲባ አቶ ኩማ በመክፈቻው ላይ ባደረጉት ንግግር ፤መንግስት አዋጁን ከመተግበር ውጪ  ሌላ አማራጭ እንደሌለውና በሊዝ አዋጁ ላይ የያዘውን አቋም ለድርድር እንደማያቀርበው መናገራቸው ነው።

አቶ መለስ ከ አስር ዓመታት በፊት በፓርላማ ሪፖርት ሲያቀርቡ፤ “መሬት አይሸጥም አይለወጥም” የሚለው የመሬት ፖሊሲ ከ አገር ልማት አንፃር የሚኖረው ጥቅምና ጉዳት በዘርፉ ባለሙያዎች  ውይይት እንዲደረግበትና አሸናፊው ሀሳብ ፖሊሲ ሆኖ እንዲወጣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ለተሰነዘረው ጥያቄ፦”በኢህአዴግ መቃብር ላይ ካልሆነ በስተቀር፤ የመሬት ፖሊሲያችን ለድርድር አይቀርብም”የሚል ምላሽ መስጠታቸው  ይታወሳል።

ይሁንና  በተጠቀሰው የአቶ መለስ ምላሽ  ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች” እርም” የተባለው መሬት እነሆ  ከአስር ዓመታት በሁዋላ   ለውጪ ባለሀብቶች በወደቀ ዋጋ  በገፍ መሸጥ መጀመሩ፤ አገሬውን እያነጋገረ ይገኛል።

የሊዝ አዋጁም  ለህዝብ ውይይት መቅረቡ፤ ቁጣና ቅሬታን ለማስተንፈስና የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ካልሆነ በስተቀር፤ እንደ ሌሎች አዋጆች በጓሮ በር ያለቀለት መሆኑ ይታወቃል።ለዚህም ነው ተሰብሳቢዎቹ የስብሰባው ፋይዳነት ሊገባቸው እንዳልቻለ ተቃውሟቸውን ያሰሙት።

አዋጅ ከወጣ በሁዋላ የ አዋጁን በጆሮ ለመንገር ነው እዚህ የሰበሰባችሁን ያሉም ነበሩ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ባለፈው ሳምንት መ ኢአድ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገኝተው ገለፃ ሲያደርጉ፦ “ኢህአዴግ ወስኖና ደምድሞ በመጣበትና ውሳኔው እንደማይታጠፍ በሚናገርበት አጀንዳ ላይ የባለ ድርሻ አካላት ውይይት እያለ ሲቀልድ እንስማለን”ማለታቸው ይታወሳል።