የአቶ አሰፋ ጨቦ የቀብር ስነ ስርአት በአዲስ አበባ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ።

ሚያዝያ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለረጅም አመታት በስደት የኖሩት አቶ አሰፋ ጨቦ በቅርቡ ባሳተሙት የትዝታ ፈለግ መፅሀፋቸው ህልም ባየሁ ቁጥር የሚታየኝ ጋሞ እና ኢትዮጵያ ናቸው ቢሉም ባደረባቸው ህመም ሳቢያ የናፈቋትን አገራቸውን ሳያዩ ከሳምንት በፊት በአሜሪካ ህይወታቸው አልፏል። የአቶ አሰፋ የቀብር ስነ ስርአት በርካታ ህዝብና ወዳጆቻቸው በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።
ታዋቂው ፖለቲከኛ፣ ጸሃፊና የህግ ሙሁር የነበሩት አቶ አሰፋ ጫቦ፣ በስራዎቻቸው በርካታ አድናቂዎችን አፍርተዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ለወጣቶች የሚሆኑ ጽሁፎችን በማጻፍ፣ ኢሳትን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ቀርበው ስለኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸውን ግንዛቤ አካፍለዋል።
በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በአቶ አሰፋ ጫቦ ሞት የተሰማውን ሀዘን በማውሳት ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸወረ መፅናናት እንዲሆንላቸው ምኚቱን ይገልፃል።