የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ፣ የወያኔ ስርዓት ባንዳዎችን የሀብት ማከማቻ ድርጅቶችን የማፅዳት ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ።

ሰኔ ፲፮( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ የሰሜን ዕዝ ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 4:00 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ ቆላድባ አካባቢ ልዩቦታው ወንፈላ በተባለው የሚገኝ የገዥው ፓርቲ ንብረት ላይ ጥቃት ፈፀሟል።
ንብረትነቱ የዳሽን ቢራ በሆነ መጋዝን ላይ በተፈፀመው በዚህ ጥቃት የኦክስጅን ጋዝ መጋዝን ከነ ሙሉ ዕቃው ሲቃጠል፣ የጂኒሪተር ክፍሉበከፊል ቃጠሎ ደርሶበታል።
ዋና መቀመጫው ጎንደር ላይ የሆነው ዳሽን ቢራ ፋብሪካ የሚያገኘው ገቢ ገዥው ፓርቲ ዜጎችን ለሚያፍንበት፣ለሚገድልበትና ለሚያሰቃይበት መሳሪያ መግዣ እና ለእስር ቤት መገንቢያ እንደሚውል ይታወቃል።
ስለሆነም በዚህ ፋብሪካ እና በመሰል የገዥው ፓርቲ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰድ ንፁሃንን ዜጎች ከመታደግም በላይ ገዥውን ፓርቲማዳከም ነው ሲል የግንባሩ ወታደራዊ ዕዝ ገልጿል።
ይህን ጥቃት የፈጸሙትት ታጋዬችም በሰላም ወደ ቦታቸው መመለሳቸውን አስታውቋል።
የነጻነት ታጋዮቹ በዚህ ሳይወሰኑ በማግስቱ ሰኔ 14 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞንበደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ጎርጎራ ክፍል በቀበሌ 01 የሚገኘውን የህወኃት ደህንነት መኖሪያ ቤት እስከነ ሙሉ ንብረቱ አውድመውታል።
ግርማይ ገብረመስቀል የሚባለው ይህ ግለሰብ ህወኃት በነጋዴ ሽፋን በደህንነት መስመር ካስገባቸው ቀንደኛው እና ዋናው ነው። በደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ይህ ጥቃት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዝኝን ኢሳት አረጋግጧል።
ግርማይ ገብረመስቀል ራሱ ብቻ ሳይሆን ሦስት ልጆቹን በዚህ የደህንነት መስመር ያስገባቸው ሲሆን፤ ሁሉም በስማቸው ተሽከካሪተገዝቶላቸው በሹፌር ሽፋን ከህወኃት መከላከያ፣ ከብሄራዊ ደህንነት መረጃ ጋር በመሆን በርካታ ንፁሃን ዜጎችንሲያፍኑ፣ሲያሳፍኑ፣ሲገድሉና ሲያስገድሉ ቆይተዋል።
ግርማይና ልጆቹ ከዚህም ባሻገር ሥርዓቱን አይደግፉም የሚባሉ ንጹሀን ዜጎችን ወደ ትግራይ ክልል፣ ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራና ወደሌሎች የተመረጡ ማሰቃያ ስፍራዎች በማጋዝ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል።
ይህ ግርማይ ገብረመስቀል የተባለ ደህንነት በነጋዴ ሽፋን ስለሚሰራ ከደንቢያ፣ከአለፋና ከደልጊ አካባቢዎች ጤፍ፣ቅቤ፣ማር፣ የእርድከብቶች፣ ደሮ እና እንቁላል ሳይቀር ያለምንም ክልከላና ፍተሻ ተፈላጊውን ግብርሳይከፍል ወደ ትግራይ እያጓጓዘ እንዲሸጥ ተፈቅዶለታል።
በቅርብ ንብረትነቱ የህወኃት ኢፈርት የሆነው መስፍን እንጅነሪግ ከአካባቢው ጤፍ ለመግዛትጨረታ ሲያወጣ ዋና አቅራቢ ከነበሩት መካከል አንዱ ይኸው በነጋዴ ሽፋን በደህንነት ተግባር የተሰማራው ግለሰብ እንደነበር ተመልክቷል።
በህብረተሰቡ ጥቆማ በደህንነት አባሉ ግርማይ ገብረመስቀል ላይ ጥቃት የፈጸሙት ታጋዮች በሰላም ወደቦታቸው መመለሳቸውም ተረጋግጧል።