የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወለድ አርሶ አደሩን እያሰደደ ነው፡፡

ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ አርሶአደሮች ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የራሱ ድርጅት ከሆነው ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በምህጻረ ቃል አብቁተ በግድ ተበድረው እንዲወስዱ በማድረጉ፣ አርሶአደሮች በወለድ አመላለስ እና በምርታመነት ችግር ምክንያት መሬታቸው እና ከብቶቻቸው እየተወረሱባቸው እንደሚገኙ እየተናገሩ ነው።
በምዕራብ አማራ በሚገኙ 73 ወረዳዎች አምና 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በግዳጅ በወሰዱት ብድር ምክንያት በ18 በመቶ ወለድ ሂሳብ ከፍተኛ ክፍያ ባለመክፈል ችግር ለእስር እና እግልት ተዳርገዋል፡፡
ማዳበሪያውን ከአብቁተ በግዳጅ ብድር ከወሰዱት ወደ 2 ሚሊዮን ከሚጠጉ አርሶ አደሮች ብድሩን ለማስመለስ እስካሁን በተደረገው ጥረት 93 በመቶ ያህሉ በእስር እና ንብረታቸው ላይ እግድ በማስቀመጥ እንዲመለስ ተደርጓል።
መንግሥት ቀደም ባሉት ዓመታት ለግብዓት መግዣ ከሰጠው ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ውስጥ 670 ሚሊዮን ብር ሳይመለስ መቅረቱን በዓመታዊ ሪፖርቱ ይፋ ያደረገው አብቁተ፣ በሚልየን የሚጠጉ አርሶ አደሮች እና የቁም ከብቶቻቸው በመኽሩ ዘመን ታሰረው እንደነበር ለዘጋቢያችን አሰተያየት ሰጠዋል፡፡