የአለማችን ቱጃር ቢልጌትስ ኢትዮጵያን ጎበኙ

መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የማይክሮሶፍት ባለቤትና ለበርካታ አመታት አለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም ሆነው የቆዩት አሜሪካዊው ቢል ጌትስ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት ቢል እና ማሊንዳ ፋውዴሽን የተባለው ድረጅታቸው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመጎብኘት ነው።

ቢል ጌትስ ኢትዮጵያ በጤናው መስክ ያስመዘገበችውን ስራ የሚመሰገን ቢሆንም፣ ብዙ መሰራት እንዳለበትም ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቢል ጌትስ የአውሮፓ መንግስትታት ለታዳጊ አገሮች የሚሰጡትን እርዳታ እንዳይቀንሱ እየተማጸኑ ነው። ሰሞኑን የኔዘርላንድ መንግስት ለደሀ አገሮች የሚሰጠውን እርዳታ ለመቀነስ ውይይት በጀመረበት ወቅት፣ ቢልጌትስ በአካባቢው ቴሌቪዥን ቀርበው ለፖለቲከኞች ተማጽኖ አድርገዋል።

ቢል ጌትስ  ፖለቲከኞች ከሀብታም አገሮች የሚለገሰው ገንዘብ የብዙ ደሀ ዜጎችን ህይወት እየታደገ መሆኑን ለማየት ከፈለጉ ከእኔ ጋር አብረው መጓዝና ማየት ይችላሉ ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ በአለም ከተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ለደሀ አገሮች የሚሰጡትን ድጋፍ ለመቀነስ እያሰላሰሉ ነው። 

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide