የተለያዩ የጸጥታ ሃይሎችን ሙሉ መረጃዎች የሚያሳዩ ሰነዶች ኢሳት ውስጥ ገቡ

ሰኔ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የጸጥታና የደህነት ሃይሎች ሙሉ ስም ዝርዝር፣ የመታወቂ ቁጥር፣ የመኖሪያና የስራ አድራሻ እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች ኢሳት እጅ ገብተዋል። የጸጥታ ሃይሎች ያደረጉዋቸውን ስብሰባዎች የሚያሳዩ ቃለ ጉባኤዎች እንዲሁም በሚስጢር እንዲያዙ የተደረጉ የምርምራ ዘገባዎችም ኢሳት እጅ ገብተዋል። ኢሳት የደህንነት ምንጮቹን አደጋ ውስጥ በማይጥል መልኩ ሁኔታዎች ሲመቻቹ ዋና ዋና መረጃዎችን እየመረጠ ለወደፊቱ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ለመግለጽ ይወዳል።