የቦረና ዞን ዋና አስተዳደር ታሰሩ

በቦረና  ዞን በጋሬና ቦረና ጎሳዎች መካከል የተሳው ግጭት የረገበ ቢሆንም፤ ችግሩ ግን አሁንም መቀጠሉን ከስፍራው የመጣው ዜና ያስረዳል። ይህንንም ተከትሎ የቦረና ዞን ዋና አስተዳደር መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ግጭቱን ተከትሎ በቦረና ዞን ግምገማ እየተካሄደ ሲሆን፤ ለግምገማው መነሻው ግጭቱን ተከትሎ በቦረና ዞን “ኢሕአዲግ አይገዛንም” የሚል ተቃውሞ በመሰማቱ ነው ተብሏል።
በቦረና ዞን ነዋሪዎች የተነሳውን ይህንን ተቃውሞ መቆጣጠር ባለመቻል ወይንም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ተባብራችኋል በሚል ከዞኑ ዋና አስተዳደር በተጨማሪ ሌሎች ባለስልጣናትም መታሰራቸውን ከስፍራው የተገኘው ዜና ያስረዳል።
በቅርቡ በሞያሌ፣ በጋሬና ቦረና ጎሳዎች መካከል በተፈጠረው የሟቾቹ ቅጥር 22 ስደርስ ከ30 ሺህ በላይ መፈናቀላቸውና ቀደጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወቃል።