የቀድሞው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፕሬዚዳንት የነበሩት የአቶ ያረጋል አይሸሹም ንብረት በፍርድ ቤት ታገደ

ኢሳት ዜና:-በአቶ ያረጋል አይሸሹምና በህወሀት ባለስልጣናት መካከል የተነሳውን የፖለቲካ ውዝግብ ተከትሎ በሙስና የተከሰሱት አቶ ያረጋል የእርሳቸውና የባለቤታቸው ንብረት እንዲታገድ ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ፣ አቶ ያረጋል በባለቤታቸው ፣ በልጆቻቸውና በእርሳቸው ስም ተመዝግበው የሚገኙ በአሶሳ በ1200 ስኩየር መሬት ላይ የሰፈረ የግል መኖሪያ ቤት፣ በዚሁ ከተማ የሚገኝ 1000 ካሬ ሜትር ቦታ፣ በቦሌ አካባቢ የሚገኘው 500 ካሬ መሬት፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚገኝ 4132 ካሬ ሜትር ቦታ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኝ 500 ስኩየር ሜትር ላይ የሰፈረ በአለ አንድ ፎቅ ህንጻ፣ የኮንዶሚኒየም ቤት፣ ምግብ ቤት እንዲሁም በልጃቸው ስም የተመዘገበ 1490 ካሬ መሬት ቦታ እንዲታገድ ወስኗል ።

አቶ ያረጋል ከህወሀት ባለስልጣናት ጋር የፖለቲካ ውዝግብ ውስጥ ባይገቡ ኑሮ በሙስና ባልተከሰሱ ነበር የሚሉ አስተያየቶች እንደሚቀርቡ መዘገባችን ይታወሳል።

የአቶ ያረጋል የሀብት መጠን በስልጣን ላይ ያሉትና የፖለቲካ ልዩነት ባለመፍጠራቸው ያልተከሰሱት የመለስ ባለስልጣኖች ምን ያክል በሙስና እንደተዘፈቁ የሚያመለክት ነው።