የህውሃት ድርጅት የሆነው ኢትዮ ችክን በአማራ ክልል ደሮ አርቢዎች ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ የክልሉ መንግስት እንዲያስቆም ተጠየቀ፡፡

ጥር ፲፯ ( አሥራ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዋና መስሪያ ቤቱ በመቀሌ ከተማ የሚገኘው ኢትዮ ችክን ከአንዳሳ ደሮ ብዜት ማዕከል የሚፈለፈሉትን ጫጩቶች ወደ ሚፈልገው አካባቢ በመጫን የሚያከፋፍል በመሆኑ ከአሁን በፊት ከማዕከሉ በመረከብ በጫጩት እርባታ የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከስድስት ዓመት በፊት በትግራይ መንግስት እና በአረብ ሃገር ባለሃብቶች ቅንጅት የተቋቋመው ኢትዮ ችክን ንብረትነቱ በህውሃት ቁጥጥር ስር ያለ ሲሆን፣ ከሃያ ዓመታት በላይ ያለ አንዳች ችግር ሲሰራ የነበረውና
አስፈላጊውን ግብዓት ለአካባቢው ወጣቶችና የደሮ አርቢ ማህበራት ሲያቀርብ የነበረውን የአንዳሳ ደሮ ብዜት ማዕከልን በማዳከም ባለፈው ዓመት በሽርክና ስም ከጠቀለለው በኋላ አጠቃላይ እንቅስቃሴውን በመቆጣጠር በክልሉ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል፡፡
በደሮ ምርት ግብዓት አቅርቦት ችግር ስራቸውን እያጡ ያሉት ወጣቶች የክልሉ መንግስት ችግራቸውን ፈጥኖ እንዲፈታላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ችግራቸው ከአንድ ዓመት በኋላም እንዳልተፈታላቸው ተናግረዋል፡፡
ከወራት በፊት ችግሩን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተናገሩት መካከል የባህር ዳር ከተማ ህዳር አስራ አንድ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆችውና ባለፈው ዓመት ዘርፉን የተቀላቀለችው ወይዘሮ ዞማ አሱባለው እንደገለጸችው በገጠማት የጫጩት አቅርቦት እጥረት ስራዋን ባቀደቸው ልክ ልታስቀጥል ባለመቻሏ በስራዋ ላይ ተጽዕኖ አሳድሮባታል፡፡
ዘርፉ አዋጭ በመሆኑ የጫጩት አቅርቦቱን በፈለገችበት ሰዓት የምታገኝበት ሁኔታ ቢፈጠር ፤በአጭር ጊዜ ሰርታ መለወጥ እንደምትችል ካለፈው ስራዋ እንዳረጋገጠች የተናገረችው ወይዘሮ ዞማ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የአንዳሳ ደሮ ብዜት ማዕከል ከተደቀነበት ተጽዕኖ በመላቀቅ የተሸሻሉ ማሽኖችን በክልሉ መንግስት አማካኝነት በማስገባት የተጠናከረ ስራ እንዲሰራ መታገዝ እንደሚገባው አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡
የአንዳሳ ደሮ ብዜት ማዕከል ተጠባባቂ ስራ አስኪያጅ አቶ ንብረት አለማየሁ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት ማዕከሉ የደሮ ብዜት ስራውን ባለፈው ዓመት ለማቋረጥ የተገደደው ከሃያ ዓመት በላይ ያገለገሉት የማስፈልፈያ ማሽኖች ሊታደሱና ሊቀየሩ ባለመቻላቸው ማዕከሉ ለትግራዩ ኢትዮ ችክን ድርጅት መተላለፉን በቁጭት ተናግረዋል፡፡
በባህር ዳር በምስራቅ ጎጃም ደጀን እና በመሳሰሉት አካባቢዎች በደሮ እርባታ ስራ ላይ የተሰመሩ በርካታ ወጣቶች ከስምንት ወር በፊት ጫጩቶቹ እ