ከዋልድባ ገዳም ታፍነው የተወሰዱት አባ ገብረኢየሱስ እስካሁን ያሉበት አድራሻ አልታወቀም

መጋቢት ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጥንታዊው እና ታሪካዊው የዋልድባ ገዳም ላይ በልማት ስም ውድመት እንዲደርስ መደረጉን በመቃወም ባለባቸው ሃይማኖታዊ ግዴታዎች ገዳሙን በመወከል ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአካልና በደብዳቤ ያቀረቡት አባ ገብረኢየሱስ በገዥው መንግስት የደህንነት አባላት ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን እስካሁንም ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም።
በገዳሙ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫዎችን ሲሰጡ የነበሩትን የአባ ገብረኢየሱስን በገዥው መንግስት የደህንነት አባላት ታፍነው መወሰዳቸውን በመቃወም ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ሰባት ነጥቦችን ያካተተ የአቋም መግለጫዎች አውጥቷል።
ሕብረቱ ታሪካዊውንና ጥንታዊውን የዋልድባ ገዳምን ከጥፋት ለመታደግ የእምነቱ ተከታዮች እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።