እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊው የሆነ ዜጋዋን አምባሳደር አድርጋ ሾመች

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ በ14 አመት እድሜው  እኤእ በ1972 ወደ እስራኤል የተጓዘው ራቻሚም ኢላዛር በኢትዮጵያ  የእስራኤል አምባሳደር ሆኖ ተሹሟል።

ራቻሚም ቴላቪቭ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በዲግሪ የተመረቀ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣ ላለፉት 30 አመታትም በጋዜጠኝነት ማገልገሉ ታውቋል።