ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ጥቃት ከመሰንዘር ይልቅ የውስጥ ችግሩን ብትፈታ ይሻላታል ተባለ

መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ጥቃት ከመሰንዘር ይልቅ የውስጥ ችግሩን ብትፈታ ይሻላታል ሲሉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ

ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የወሰደችው ወታደራዊ ጥቃት በአገር ውስጥ የሚታየውን ችግር ለመሸፋፈን ተብሎ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ የግል አስተያየታቸውን ለኢሳት ተናግረዋል።

ዶ/ር ነጋሶ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ በወሰደችው ወታደራዊ እርምጃ መደንገጣቸውን ተናግረው ፣ ኤርትራ ትረዳቸዋለች የሚባሉትን የኢትዮጵያውያን አማጺዎችን ችግር ለመፍታት ፣ በቅድሚያ በአገር ውስጥ ያለውን ችግር መፍታት ይገባል ብለዋል

ብዙ የውስጥ ችግሮች አሉ የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ እነዚህን ችግሮች ሳይፈቱ ወደ ጦርነት መግባት በአገሪቱ ላይ አሁን የሚታዩትን ችግሮች የበለጠ የሚያባብስ ነው የሚሆነው።

ዶ/ር ነጋሶ መንግስታት የውስጥ ችግሮች ሲበዙባቸው የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር እንዲህ አይነት ስልት መጠቀም የተለመደ ነው ብለዋል።

የመለስ መንግስት በኤርትራ ወታደራዊ ተቋማት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን መግለጡ ይታወሳል። ኤርትራ የህወሀት መንግስት   በአገር ውስጥ ያለበትን ችግር ለመሸፋፈን ብሎ የወሰደው፣ ትኩረት የማስቀየሻ መንገድ ነው በማለት መናገሩዋና አጸፋዊ መልስ እንደማትሰጥ መግለጡዋ ይታወሳል።

የምእራባዊያን መንግስትታ ሁለቱ አገሮች ወደ ሙሉ ጦርነት እንዳይገቡ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው። በአፍሪካ ጉዳይ ቀዳማይ ወኪል ነኝ የሚለው ጥርስ አልባው የአፍሪካ ህብረት ጥቃቱን አስመልክቶ  እስካሁን ያለው ነገር የለም።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide