ኢትዮጵያዊው የረዥም ርቀት ሯጭ በድራግ ምክንያት ታገደ

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሌላ በኩል በሮም በተካሄደው የ 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ፋንቱ ማንጌሶ በአስደናቂ ሁኔታ ውድድሩን በማሸነፍ በተመልካቾችና በኮሜንታሮች ዘንድ ልዩ አድናቆትን  ጭራለች።

እንደ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ  አትሌት ህዝቅያስ ሢሳይ ለሁለት ዓመታት ከማናቸውም ውድድሮች የታገደው ባለፈው ዓመት በተካሄደው እና ዘጠነኛ ሆኖ ባጠናቀቀበት የኒውዮርክ ማራቶን ላይ   ኤሪትሮፖቲን ወይም በምህፃረ-ቃሉ ኢፒኦ ተብሎ የሚጠራቀውን ሀይል ሰጪ ድራግ ወስዶ መሳተፉ በሐኪም ምርመራ በመረጋገጡ ነው።

ዓለማቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የዩናይትድስቴትስ  የፀረ-ድራግ ግብረ-ሀይል ኤጄንሲ በበኩላቸው፤ሢሳይ  ለስፖርተኞች ክልክል የሆነውን ኢፒኦ የተባለ ንጥረ-ነገር እንደወሰደ ማመኑን እና የተጣለበትን እገዳ በፀጋ መቀበሉን ገልፀዋል።

የ 24 ዓመቱ  ወጣት አትሌት ሢሳይ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ባለፈው ኖቬምበር 6  በኒዮርክ በተካሄደው ማራቶን 9ኛ ሆኖ ካጠናቀቀ በሁዋላ በተደረገለት የደም ምርመራ ነው ኢፒኦ ወስዶ መገኘቱ የተረጋገጠው።

የእገዳው ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ከተመረመረበት ቀን ጀምሮ ሲሆን፤ በኒውዮርኩ ማራቶን ያገኘውም ሆነ ከዚያ በፊት ያስመዘገባቸው ውጤቶች ሁሉ እንደሚሰረዙበት ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ታሪክ፤ አንድ ኢትዮጵያዊ አትሌት ለስፖርተኞች የተከለከለን ንጥረ-ነገር  መውሰዱ ሢሰማ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በሌላ በኩል በሮም በተካሄደው የ 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ፋንቱ ማንጌሶ በአስደናቂ ሁኔታ ውድድሩን በማሸነፍ በተመልካቾችና በኮሜንታሮች ዘንድ ልዩ አድናቆትን  ጭራለች።

ውድድሩ እንደተጀመረ ሩማኒያዊቷ አንድሪያኖቫ ከሁሉም አትሌቶች በፍጥነት ሩጫ ተለይታ በመውጣትና  ለጥቂት ዙሮች በረዥም ርቀት ልዩነት  በመምራት ሜዳውን ተቆጣጠረችው።

ይሁንና አንድሪያኖቫ  ሩጫዋን አቋርጣ ለመቆም የተገደደችው ውድድሩ ገና ከግማሽ ብዙም ሳያልፍ ነበር።

ውድድሮች ሲጀመር አፈትልኮ በመውጣት በረዥም ርቀት ከመራ በሁዋላ ወደ መሀከል ላይ አቋርጦ የሚወጣው ኢትዮጵያዊ አትሌት በቅፅል ስሙ፦”ሾላ” ተብሎ እንደሚጠራ ይታወቃል።

የሮሙን ውድድር በቴሌቪዥን መስኮት የተከታተሉ እና በቲዩቦች የተመለከቱ ኢትዮጵያዊያን፦ አንድሪያኖቫን፦” ሾላ” ሲሏት ተደምጠዋል።

አንድሪያኖቫ አቋርጣ ከወጣች በሁዋላ  በቀሪዎቹ አትሌቶች ፉክክሩ  ቀጠለ።

ውድድሩ አንዱ ዙር እሰከሚቀረው ድረስ እጅብ ብለው ሢሮጡ ከነበሩት አትሌቶች መካከል ዕውቋ ከንያዊት አትሌት ፓሜላ ጄሊሞ ተለይታ በመውጣት ወደ ፊት ስትገሰግስ ሁሉም-  ያለ ጥርጥር  የወርቁ ባለቤት እሷ እንደሆነች ገመቱ።

ዓይኖች ሁሉ በጀሊሞ ላይ ባፈጠጡበት ሰዓት አረንጓዴ ቲ-ሸርት በጥቁር ቁምጣ የለበሰች ጠይም አትሌት  እንደተወርዋሪ ኮከብ እየተምዘገዘገች ከሁዋላ ተፈትልካ ወጣች።

“ፓሜላ..” እያሉ ስለ ኬንያዊቱ አትሌት ማሸነፍ በእርግጠኝነት እየተቀባቡ ሲያወሩ የነበሩት ኮሜንታተሮች ፦”ኢትዮጵያዊቷ ማጊሶ መጣች..ኢትዮጵያ…ኢትዮጵያ…” ማለት ጀመሩ።

ፋንቱ  እየባሰባት መጣች። ፍጥነቷን ጨመረች። ልክ ውድድሩ ሊጠናቀቅ መቶ ሜትር ሲቀር ካሜላን ደርባ በማለፍ እንደ አቦ ሸማኔ ተወነጨፈች።ጋዜጠኞችንም፣ታዳሚዎችንም ባስደነቀ ልዩ ሁኔታ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጀች።

ፋንቱ ወድድሩን ያጠናቀቀችው በ 1 ደቂቃ 57. 56 ሰከንድ ሲሆን፤ይህም በኢትዮጵያ የመቶ ሜትር ውድድር ታሪክ የመጀመሪያው ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል። የዓለም ሳይሆን-የኢትዮጵያ ሪከርድ።

ፋንቱ በሮም ይህን  ድል በመቀዳጀቷም፤  በጎልደን ሊግ ውድድር ከኬኒያዊቷ ካሜላ ጋር ተካታለች።

ፋንቱን እና ካሜላን በመከተል ሦስተኛ የወጣችው ሩሲያዊቷ ማሪያ ሳቪኖቫ ስትሆን፤የብሪታኒያዋ ኢማ ጃክሰን  ውድድሩን 2፡00 ከ 08 ሰከንድ በማጠናቀቅ 10 ኛ ወጥታለች።

በእንግሊዛዊቷ ውጤት ያዘነው ቢቢሲ፦”ጃክሰን ከተወዳዳሪዎቹ  አንድኛቸውን እንኳን ማሸነፍ አልቻለችም ” ብሏል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide