ኢትዮጵያን ለቀው የሚወጡ ዜጎች ቁጥር በታሪክ ታይቶ በማይታወቅበት ደረጃ ላይ መድረሱ ታወቀ

ኢሳት ዜና:- የኢሳት የባህርዳር ዘጋቢ እንዳለው በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን በመልቀቅ ወደ የመንና ሱዳን የሚሰደደው ህዝብ በእጅጉ አስደንጋጭ ሆኗል።

የአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ባለስልጣናት ያቀረቡትን ሪፖርት ተንተርሶ በላከው ዘገባ ተሰዳጆቹ የከተማ ነዋረዎች ብቻ ሳይሆኑ ገበሬዎች ጭምር ናቸው።

በደቡብ ጎንደር በየሳምንቱ ከ250 እስከ 300፣ በሰሜን ወሎ ከ300 እስከ 450 ፣ በደቡብ ወሎ ከ200 እስከ 300፣ በጎጃም ከ400 እስከ 550 የሚደርሱ ገበሬዎችና የከተማ ነዋሪዎች ወደ የመን፣
ሱዳንና ሌሎች የጎረቤት አገሮች በገፍ ይሰደዳሉ።

ለስደቱ ዋነኛ ምክንያቶች ተደርገው የተቆጠሩት በየጊዜው የሚጨምረው የኑሮ ውድነት እና የእርሻ መሬት ጥበት ነው።

የህዝብ ቁጥር እየጨመረ፣ ተጨማሪ መሬት እየጠፋ፣ ያለውም መሬት ቢሆን ለውጭ ባለሀብቶች እየተሰጠ መሆኑ ችግሩን እንዳባባሱት ተጠቁሟል።