ኢሳት የ7ኛ አመት ምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በሲልቨርስፕሪንግ የተሳካ ገቢ ማሰባሰቢያ አካሄዱን አስታወቀ

ኢሳት (ሚያዚያ 30 ፥ 2009)

የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን (ኢሳት) የ7ኛ አመት ምስረታን በማድረግ በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ የተካሄደው የገቢ ማሳሰቢያ የተሳካ እንደነበር አስተባባሪዎች ገለጹ።

የዋሽንግተን ዲሲ የኢሳት ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ያዘጋጀው የ7ኛ አመት የምስረታ በዓል በድምቀት መከበሩን ለማወቅ ተችሏል። 

በስነ-ስርዓቱ ታዋቂዎቹ ድምጻውያን ሻምበል በላይነህ እና ደሳለኝ መልኩ ኮሜዲያን  ወንደወሰን ( ዶክሌ) ታዳሚዎችን ሲያዝናኑት አምሽተዋል።

የኢሳት 7ኛ አመት የምስረታና የገቢ ማሰባሰቢ
ያ ዝግጅቱ ላይ የድርጅቱን ውጣ ውረድ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ ለእይታ በቅቷል።

የኢሳት ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ ገላው በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ዕምቢተኝነት ከፍተኛ ሽፋን በመስጠት በኢትዮጵያ ነጻነት እንዲመጣ የተደረገውን እንቅስቃሴ አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ በአገዛዙ የሚደርሰውን ግፍና በደል በማጋለጥ ኢሳት የማንቂያ ደወል ሆኖ ማገልገሉንም አቶ አበበ ገላው ለታዳሚዎች ገልጿል።

የዝግጅቱ ታዳሚዎች በጨረታ በመሳተፍ ለኢሳት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርጉ ውለዋል። ኢሳት የህዝብ ድምፅ በመሆኑ የሚሰጠውን አገልግሎት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ያላቸውን ከፍተኛ ድጋፍ አሳይተዋል።