ኢሳትን ለመደገፍ በቦስተን የተዘጋጀው የእራትና የመዝናኛ ምሽት የተሳካ እንደነበር ኮሚቴው አስታወቀ

ጥር 9 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-የኢትዮጵያ የገና በአልን በማስመልከት እና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳትን) ለመደገፍ በቦስተን የተዘጋጀው የእራትና የመዝናኛ ምሽት በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት እና ኢሳትንም ለመደገፍ በርካታ ገንዘብ የተሰበሰበበት እንደነበር ኮሚቴው አስታወቀ
አርቲስት ታማኝ በየነ በሚታወቅበት ተመልካቾቹን በተለያየ ስሜት ውስጥ በሚከተው በቭድዮ መረጃዎች እና ቀልዶች በሚዋዛው ንግግሩ ሃገራችን ያለችበትን ሁኔታ ለዝግጅቱ ታዳሚዎች አስረድቷል! ንግግሩን የጀመረው ቦስተን በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እጅግ በጣም በሚወደደው በአርቲስት ሻምበል በላይነህ ገጠመኝ ነበር::
አንድ ኢትዮጵያዊ አንጋፋው አርቲስት ሻምበል በላይነህን አንድ ቀላል ጥያቄ ይጠይቀዋል "ፕላንህ ምንድን ነው?" ሻምበልም "እኔማ ፕላኔ በአንድ እጄ መስንቆዬን በአንድ እጄ ጠብ-መንጃዬን ይዤ ወያኔን መዋጋት ነው!" ብሎ በፈርጣማ ቃላቶች በኩራት ይመልሳል:: ጠያቂውም በመደናገጥ " እረ ሻምበል እኔ እኮ የጠየኩህ የስልክህን ፕላን ነው!" ማለቱ በማውሳት ታዳሚውን አስቆታል።
ኣርቲስት ሻምበል በላይነህና የቦስተኗ  ድምጻዊት ቤቴልሄም መላኩ የቦስተንን ህዝብ እጅጉን ባስደሰተው የሙዚቃ ዝግጅት ታማኝ በየነም በመቀላቀል በአሉን ከተጠበቀው በላይ ድምቀት ሰጥተውታል
በቦስተን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ጊዜ ለሃገራቸው በሚያደርጉት አስተዋጾ የሚደነቁ ሲሆኑ: በዚህ ምሽት ላይም በራሱ መንግስት ታፍኖ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ አለኝታ ለሆነው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን የተቻላቸውን እርዳታ ለግሰዋል::
ይህ ዝግጅት የተዘጋጀው በወጣቶች በሚመራው የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ቦስተን ሲሆን: በዝግጅቱ ላይ የነበሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን : ወጣቶቹ ባሳዩት የሃገር ተቆርቋሪነትና የሃገር ሃላፊነትን የመረከብ የተደራጀ እንቅስቃሴን እድንቀዋል::