ኢህአግ፤ ወታደራዊ ድል ተቀዳጀሁ አለ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሚያዝያ 28 ቀን 2004 ዓመተ ምህረት  በሰሜን ጎንደር ዞን በሰሮቃ ልዩ ስሙ እምቡጉዳድ በሚባል ስፍራ ከወያኔው ልዩ ሀይል ጋር ባካሄደው አውደ ውጊያ ዘጠኝ ወያኔ ገድሎ ሶስት ማቁሰሉን ገለጸ።

ግንባሩ  ጥቃቱን ከመፈፀምም ባሻገር  እንቅስቃሴውን በአካባቢው በማስፋፋት ህዝቡን የሚቀሰቅሱ በራሪ ወረቀቶችን ማሰራጨቱንም አስታውቋል።

በግንባሩ የተበተኑት ወረቀቶች ከያዙት መልእክቶች ውስጥ፦በዋልድባ ገዳምና በተለያዩ የሀይማኖት ተከታዮች ላይ ለከት የለሽ ጥቃት በሚሰነዝረው ወያኔ ላይ ተነስ!፣ኢትዮጵያዊነት መንፈስና ስሜትን ለማጥፋት በሚባዝነው ጎጠኛ ላይ ተነስ! የሀገሪቱን ሀብት ጥቅልሎ በመያዝና በመበዝበር ህዝቡን በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ችግር እንዲሰቃይ በዳረገው የጸረ-አንድነት ቡድን ላይ ተነስ” የሚሉት ይገኙበታል።!

ይህ በእንዲህ እንዳለ… የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን በርካታ ምልምሎቹንሰሞኑን ግንቦት 5 ቀን 2004 ዓመተ- ምህረት አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካክል ሴቶችም የሚገኙበት ሲሆን፤ የተሰጣቸውን ስልጠና በብቃት ተከታተለው መጨረሳቸው ታውቋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide