ኢህአዴግ በ3 ዙር 2 ሺ ካድሬዎችን ሊያሰለጥን ነው

ግንቦት ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ በመግባቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ከፍተኛና መካከለኛ ካድሬዎችን የቀነሰው ኢህአዴግ ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ መስተዳደርና ከ9 ክልሎችና የፌደራል መስሪያ ቤቶች የመለመላቸውን 500 የሚሆኑ ካድሬዎችን ግንቦት 14 ቀን 2009 ዓም አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት የሚያስመርቅ ሲሆን፣ በስልጠና የቆዩት ካድሬዎች ስለጨበጡት ትምህርት ፈተና እንደሚፈተኑ እንደሁም በሚቀጥሉት ቀሪ 3 ዙሮች ተመሳሳይ ስልጠና እንደሚሰጥ የአዲስ አበባው ወኪላችን ዘግቧል።
በአጠቃላይ በሚኖረው 4 ዙር ስልጠና 2 ሺ ካድሬዎች ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን፣ ማንኛውም ወጪያቸው ከመንግስት ካዝና ወጪ እንደሚደረግ የድርጅቱን ምንጮች በመጥቀስ ዘግቧል፡፡