አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 8.7 በመቶ ማደጉን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2009)

በኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ መጨመረን ተከትሎ የሃገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 8.7 በመቶ ማደጉን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ረቡዕ አስታወቀ።

በግንቦት ወር የምግብ ነክ ሸቀጦችን ግሽበት 12.3 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፣ በሚያዚያ ወር ግሽበቱ 12.2 እንደነበር ሮይተርስ የኤጀንሲውን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጣሸቀጦች ግሽበት ባለፈው ወር ከነበረበት 4.6 በመቶ ወደ 4.7 በመቶ ከፍ ማለቱም ታውቋል።

በምግብና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጣሸቀጦች ላይ የታየው ይኸው የዋጋ ንረት፣ አጠቃላይ የዋጋ ንረቱ እያደገ እንዲሄድ ምክንያት መሆኑን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ እንዲሁም ሃገሪቱ አጋጥሟት ያለው የፋይናንስ ቀውስ የዋጋ ጭማሪ እንደተመዘገበ አስተዋጽዖ ማድረጉን የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይገልጿል።

የአለም ባንክና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ኢትዮጵያ አጋጥሟት ያለው የውጭ ንግድ መቀነስና የውጭ ምንዛሪ መሆኑን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ እንዲሁም ሃገሪቱ ያጋጠማት የፋይናንስ ቀውስ የዋጋ ጭማሪ እንዲመዘገብ አስተዋጾኦ ማድረጉን የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

የአለም ባንክና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ኢትዮጵያን አጋጥሟት ያለው የውጭ ምንዛሪ መቀነስ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት ለዋጋ ግሽበት ምክንያት እንደሚሆን ሲያሳስቡ ቆይተዋል።

በአስመጪነት ንግድ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ባለሃብቶች የውጭ ምንዛሪ ማግኘት በመቸገራቸው ከውጭ ሃገር በሚገቡ የምግብና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጣሸቀጦች ላይ እጥረትና የዋጋ ንረት እየጨመረ እንዲሄድ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።

እነዚሁ አስመጪ ነጋዴዎች የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት በትንሹ ስድስት ወር እንደሚጠብቁ ይገልጻሉ።

የሚፈልጉትን ያህል የውጭ ምንዛሪ ባለማግኘታቸው ሳቢያ የንግድ ስራቸው ክፉኛ መጎዳቱን እና ለግብር እዳ መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

በጤፍ ስንዴ በቆሎ ማሽላ፣  ስጋ ዋጋዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ተጠቃሚዎች ገልጸዋል።

የአለም ባንክ በበኩሉ ኢትዮጵያ ያጋጠማት የፋይናንስ ቀውስ እና የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ ማሻሻያን ማድረግ እንዳለባት አሳስቧል።

ለተከታታይ አራት አመታት መዋዠቅ ያሳየውን የውጭ ንግድ ገቢን ለመታደግም ሃገሪቱ ብር ከዶላር ጋር ያለውን የመግዛት አቅም መቀነስ እንዳለባት ሃሳብን ቢያቅርብም፣ የመንግስት ባለስልጣናት ሃሳቡ ከቅጥሙ ጉዳቱ ይበልጣል በሚል ተግባራዊ እንደማይሆን ምላሽ ሰጠዋል።