አዲግራት ዩኒቨርስቲ በፌደራል ፖሊሶች ተከቧል

ጥር ፲፰ ( አሥራ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ የትምህርት ቤቱ ቤተመጽሃፍ፣ መዝናኛ ክበብና አዳራሾች መስታውቶቻቸው ተሰባብረዋል። ነገ የማጠቃለያ ፈተና እንደሚሰጥ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በተቃውሞው ምክንያት ፈተናው አይሰጥም። ትናንት በርካታ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደብድበዋል።