አቶ ንዋይ ገብረአብ ለአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽነርነት ታጩ

ሰኔ ፲፱( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃቱ ባለስልጣን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅትን እንዲመሩ በተመረጡ 2 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፣ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ አቶ ንዋይ ገብረአብን ለአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ቦታ በእጩነት አቅርቧል። የአፍሪካ ህብረት ሹመት በመንግስታት ድጋፍ የሚገኝ በመሆኑ፣ አቶ ንዋይ ቦታውን የመውሰድ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ህወሃት አዲስ አበባ በገባ በአመቱ የአቶ መለስ ዜናዊ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው የሰሩት አቶ ንዋይ፣ እስካለፈው አመት ድረስ በዚሁ ሃላፊነታቸው ሰርተዋል።