አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በእስራኤል ድንገተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው

ግንቦት ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በአገራቸው ጉዳይ ላይ ለማነጋገር ወደ እስራኤል የተጓዙት አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ያልታሰበ ድንገተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው። የህወሃት/ኢህአዴግ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎችን ለይቶ በሚስጥር በመጥራት ለማወያየት ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ተሰብሳቢዎች በስም ጥሪ እንዲገቡ ተደርገዋል። በአገራችን ጉዳይ ያገባናል ያሉ ዜጎች ወደ ስብሰባው አዳራሽ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው ሲሆን አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸውም ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ገልጸዋል።
የስርዓቱ አገልጋይ የሆኑ የሃይማኖት አባቶች ወደ ስብሰባ አዳራሹ ሲገቡ ለገጠማቸው ተቃውሞዎች በምልክት ጭምር ጸያፍ ግብረመልስ ሲሰጡም ተስተውሏል። የተቃውሞ አስተባባሪ የሆኑት ወጣቶች በበኩላቸው ይህን አንባገነን ስርዓት በጋራ በሆን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ታግለን መጣል ይገባናል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።