የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት የተመሰረተባቸው ክስ በአሸባሪነት የሚያስጠይቅ አይደለም ተባለ

ህዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የልደታ ፍ/ቤትና አካባቢው በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ የሀወዝብ ብዛት ተጨናንቆ ማርፈዱም ተዘገበ።

ዛሬ በልደታ ፍ/ቤት የቀረቡት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ በአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው 29 ሙስሊሞች ላይ አቃቢ ህግ የመሰረተው ክስ ተከሳሾቹን በአሸባሪነት አያስከስሳቸውም ሲሉ የተከሳሰሾቹ ጠበቆች አያስከስሳቸውም ያልዋቸውን ነጥቦች ለፍ/በቱ አቅርበዋል።

በአሸባሪነት ህጉ አንቀፅ 3 እና 4 ተቀውሞአቸውን ያሰሙት የተከሳሾቹ ጠበቆች ለዲናችን እንሞታለን ማለታቸው አሸባሪ አሰኝቶ በአሸባሪነት ሊያስከስሳቸው አይችልም ይህ ቁራናዊ መርህ በመሆኑ ቃሉን መጠቀም አሸባሪነት አይደለም በማለት የአቃቢ ህግን ክስ ተቃውመዋል።

ያለም አቀፍ ያሸባሪነት ህግ በአሸባሪነት የተጠረጠረ ሰው ቤቱ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ይፈተሻል እንደሚል ለፍ/ቤቱ ያመለከቱት የተከሳሾቹ ጠበቆች የኢትዮጵያው ህግ ግን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤቱ ይፈተሻል መለቱና የህንን መሰረት ተደርገው የተወሰዱ እርምጃዎች አግባብ አለመሆናቸውን የተከሳሽ ጠበቆች ለፍ/ቤቱ ተቃውሞና ጥያቄያቸውን አቅርበዋል ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የመሪዎቻቸውን የፍርድ ሂደት ለመከታተል ከጥዋቱ 2 ሰአት ጀምሮ በልደታ ፍርድ ቤት የተገኙ ሲሆን ወደ ችሎቱ እንዳይገቡ በመታገዳቸው የልደታ አካባቢ ከታች እስከ ኮካ ከላይ እስከ አብነት መንገድ በህዝብ ብዛት መንገዱ ተዘግቶ እስከቀኑ ስድስት ሰአት ተኩል መዝለቁ ተዘግቦል::

ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች በሙስሊሙ መሀከል ገብተው ብጥብጥ ለማስነሳት መሞከራቸውን የገለጹልን የኢሳት ምንጮች ይህ አልሳካ ሲላቸው ሰው ይዘው ለመሄድ ቢሞክሩም ህዝቡ በቆራጥነት አላስነካ እንዳላቸው ገልጠዋል::

በልደታ ፍርድ ቤት አካባቢ ሱቆችና ካፍቴርያዎች በፌደራል ፖሊሶች ትእዛዝ የተዘጉ ሲሆን የአካባቢው ባንክም ለግማሽቀን ስራ እንዳይሰራ መደረጉ ተነግሮል::

የዛሬው የልደታ ፍርድ ቤት ታዳሚ ልክ በቃሊቲው የጉብኝት ጉዞ እንደታየው ፍጹ ቆራጥነት የታየበት ነበር ያሉት ምንጮቻችን ሴቶችና እናቶች ሳይቀሩ የፌደራል ፖሊሶች ሊያባርሮቸውና  ሲሞክሩ መግደል ጀምራችሆል ግደሉን እንጂ አንድ እርምጃ ወደሆላ አንሄድም በማለት ተጋፍጠዋቸዋል::

ዛሬ ያስቻለው ፍርድ ቤት የተከሳሽ ጠበቆችን ቃል ከሰማ በሆላ ለህዳር 21 ቀጠሮ ሰቶ መበተኑን ለማ ተችሎል::