አስራ ሁለት ሺ ኢትዮጵያውያን በሱዳን ታሰሩ

የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ታዲያስ አዲስን በመግለጽ የዘገበው ደብረብርሀን ብሎግ ፣ በሰሜን ሱዳን ውስጥ በሚገኘው ኦምዱርማን እስር ቤት ውስጥ 12 ሺ ኢትዮጵያውያን ታስረው ይገኛሉ።

ምንም እንኳ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን ያለ ህጋዊ ሰነድ ወደ ሱዳን  የገቡ ናቸው ቢባልም፣ ህጋዊ ወረቀት የያዙት ሳይቀር መታሰራቸው ተዘግቧል።

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያውያን ችግሩን በሱዳን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሲያመለክቱ ኢምባሲው  “አያገባኝም ” የሚል መልስ መስጠቱ ታውቋል።

እንደታዲያስ አዲስ ዘገባ በምርመራ የኤች አይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የተገኘባቸው ኢትዮጵያውያን በመርዝ እንዲገደሉ ይደረጋሉ። በእስር ላይ በሚገኙት ሴት ኢትዮጵያውያንም ላይ የወሲብ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸውም ተዘግቧል።

የአዲሱ የእስር ዘመቻ የሁለቱ አገራት መንግስታት በቅርቡ ለጸጥታ አደገኛ ናቸው የሚሉዋቸውን ስደተኞች ለመለዋወጥ ካደረጉት ስምምነት ጋር ሊያያዝ ይችላል ተብሎአል።

የመለስ መንግስት የሱዳንን ጂኦ ስትራቴጂክ ጠቀሜታ ስለሚረዳ ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የገዢው ፓርቲ ደጋፊ እንዲሆኑ፣ ካልሆነው ወደ ተቃዋሚዎች ጎራ ተቀላቅለው ጥቃት እንዳይፈጽሙበት ለማድረግ አበክሮ እንደሚሰራ ሱዳን ውስጥ ተቀማጭ የሆኑት አቶ አበባው ማንደፍሮ ገልጠዋል።

በአሁኑ ጊዜ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው አቶ አበባው አክለው ተናግረዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide