አርቲስት ደበበ እሸቱ ከእስር ተለቀቀ

ህዳር 2 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሽብር ወንጀል ተከሶ ለአለፉት አምስት ወራት በእስር ላይ ይገኝ የነበረው አርቲስ ደበበ እሸቱ ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ መንገድ መፈታቱ ታወቀ።

አርቲስ ደበበ ከጠበቃው ጋር እንዳይገናኝ ተደርጎ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።

አርቲስቱ አርብ ህዳር 1 ቀን 2004 ዓም ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ በፌደራል ፖሊሶች ታጅቦ ወደ ቤቱ መወሰዱንና ቤተሰቦቹ እንዲረከቡት መደረጉን
በስፍራው አብረውት የነበሩ ወዳጆቹ ለኢሳት ተናግረዋል።

አርቲስት ደበበ አካላዊ ጉስቁልና እንዳጋጠመው ለመረዳት ቢቻልም መንፈሱ ግን አሁንም ጠንካራ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

አርቲስ ደበበ በምን ሁኔታ እንደተፈታ ጓደኞቹ ሲጤኢቁት ምናልባት በስም ሞክሼ ያሰሩኝ ይመስለኛል በማለት መቀለዱን ለማወቅ ችለናል።

የአርቲስ ደበበ እሸቱ በሽብር ወንጀል መከሰስ የመለስን መንግስት የአለም መሳቂያ አድርጎት እንደነበር ይታወሳል።