አርበኞች ግንቦት7 ተጨማሪ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ለኢሳት በላከው መረጃ እንደገለጸው ግንቦት 7 ከሌሊቱ 8 ሰአት ከ55 ደቂቃ ላይ ሲሆን በደቡብ ጎንደር ዞን በሊቦከምከም ወረዳ በጣራ ገዳም አካባቢ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ጦሩ በተጠቀሰው ቦታ ላይ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ስቃይ ሲፈጽም እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል።
የንቅናቄው ታጋዮች ወደ ወታደሮች ምሽግ በመግባት 8 ወታደሮችን መግደላቸውንና አንድ ወታደር ማቁሰላቸውን፣ በድጋሜ 5 ሰአት ላይ በተደረገ ውጊያ ደግሞ 5 ገድለው 3 ማቁላቸውን ገልጸዋል።
በራሱ በኩል አንድ ታጋዩ መቁሰሉንና የሞተ አባሉ እንደሌለም መግለጫው አመለክቷል። ንቅናቄው አገኘሁት ስላለው ድል ከገዢው ፓርቲ በኩል የተሰጠ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ የለም።