አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ በዋሽንግተን ዲሲ ዝግጅት ያቀርባሉ

ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ “ለመብት ተማጓቾች ይጻፉ” በሚል ርእስ በዋሽንግተን ዲሲ ናሽናል ፕሬስ ክለብ አንድ ዝግጅት  ያቀርባሉ።

ዲሰምበር 9፣ 2011 በሚቀርበው ዝግጅት  ላይ የቀድሞ የአንድነት ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በክብር እንግድነት ይገኛሉ።

ከ6፡30 እስከ 9፡30 በሚቆየው ዝግጅት ኢትዮጵያኖች ተገኝተው በእስር ላይ ለሚገኙት የነጻነት ታጋዮች ደብዳቤ እንዲጽፉ የአንድነት ዲሲ ሜትሮ የድጋፍ ቅርንጫፍ ጠይቋል።