አሜሪካዊው ጂም ኦንግ ኪም አዲሱ የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኮሪያዊው አሜሪካዊው የጤና ኤክስፐርት የሆኑት ጂም ዮንግ ኪም በምርጫ ውድድሩ ወቅት የናይጀሪያዊዋ የፋይናንስ ሚኒሰትር ከሆኑት ሚስ ኒጎዚ ኦኮንጆ ኢዊአላ ከፍተኛ ፉክክር ገጥሞአቸው ነበር። በስልጣን ላይ ያሉትን ሮበርት ዞሊክን የሚተኩት የ52 አመቱ ኪም ፣ በደሀ አገሮች ውስጥ የተስፋፉትን የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትና የቲዩበር ክሎሲስ በሽታዎችን ለመዋጋት ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ተነግሯል።

የአለም የገንዘብ ድርጅት በምጻረ ቃል አይ ኤም ኤፍ እና የአለም ባንክ ከተመሰረቱበት እኤአ ከ1944 ጀምሮ የመሪነቱን ስፍራ አውሮፓውያን እና አሜረካዊያን ይዘውት ቆይተዋል። ናይጀሪያዊቷ አዊአላ አሸንፈው ቢሆን ኖሮ የመጀመሪያዊቷ ጥቁር የባንኩ ፕሬዚዳንት ይሆኑ ነበር።

የአቶ መለስ ዜናዊ ወዳጅ ተደርገው የሚታወቁት ጆሴፍ ስትገሊቲዝ ራሳቸውን በእጩነት አቅርበው ነበር፤ ሆኖም ምንም ድጋፍ ለማግኘት ሳይችሉ በመቅረታቸው ራሳቸውን ከውድድር በጊዜ አሰናብተዋል።

________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide