ነዋሪዎች በላያቸው ላይ ቤቶች እንደፈረሱባቸው ተናገሩ።

የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ሰኞ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አፍራሽ ግብረሃይል ከ500 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን አፍርሷል። ታዛቢዎች እንደሚናገሩት አፍራሽ ግብረሃይሉ በድንገት በመሄድ በወሰደው እርምጃ 2 ከወለዱ ሳምንት ባልሞላቸው እናቶች ላይ ቤታቸውን በላያቸው ላይ አፍርሰዋል። እርጉዞች ፣ ህናጻትና አሮጊቶች በተወሰደው እርምጃ ሲያነቡ አርፍደዋል።
እቃቸውን እንኳ በወጉ እንዳያወጡ በመደረጋቸው ብዙዎች ለአመታት ደክመው የገዙዋቸውን እቃዎች ሳይቀር አጥተዋል። በአዲስ አበባ በተለያዩ ወረዳዎች በሚወሰዱ ተመሳሳይ እርምጃዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ይፈናቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እስከዛሬ ድረስ በተካሄድ የማፈናቀል ዘመቻ በርካቶች ፣ ለጎዳና ተዳዳሪነትና ለከፋ ድህነት ተደርገዋል።