በጉጂ ኦሮሞዎቸና በደቡብ ክልል ልዩ ሃይል መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ሰዎች ተገደሉ

ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ከሁለት ቀናት በፊት የጉጆ ኦሮሞዎች ከብት መወሰዱን ተከትሎ በኮሬ ማህበረሰብና በጉጂ ኦሮሞዎች መካከል ግጭት ቢነሳም፣ የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ጣልቃ በመግባትና በጉጂዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር 3 የጉጂ ብሄረሰብ አባላት ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ወደ ቡሌ ሆራ ሆስፒታል ተወስደዋል። ግጭቱ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ቀጥሎአል።