በጃዊ የነጻነት ሃይሎች ከስርዓቱ ወታደሮች ጋር እየተዋጉ ነው

ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል አዊ ዞን ከአገዛዙ ጋር የሚፋለሙ የነጻነት ሃይሎችን ለመውጋት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት እየተንቀሳቀሰ ነው።

የአይን እማኖች እንደገለጹት ትናንት በጃዊ አድርጎ አንድ ታንክ በሎቤድ ተጭኖ ተዋጊዎቹ ይገኙበታል ተብሎ ወደ ሚገመተው ሱዋታ ወይም አይማ ተንቀሳቅሷል። አይማ በደቡብ ምእራብ ቋራና ሰሜን ጃዊ ወረዳ የሚገኝ ቦታ ሲሆን፣ ከታንኩ ጋር በርጃታ የአገዚ ወታደሮች ወደ አካባቢው ተንቀሳቀስዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት እስካሁን ድረስ በዚህ ግንባር የሄደ የስርዓቱ ወታደር ወይ ይሞታል ወይም እጅ ይሰጣል።

በጃዊ ስለሚደረገው ውጊያ በአገዛዙ በኩል እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።