በዋልድባ ገዳም አካባቢ ማይጋባ በሚባል ቦታ ላይ በፌደራል ፖሊስና እና በአርሶ አደሩ መካከል በተነሳ ግጭት 15 ሰዎች ተገደሉ

ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ግጭቱ የተነሳው ግንቦት25 ሲሆን፣ የፖሊስ አባላቱ የአካባቢው አርሶአደሮች ቤቶቻቸውን እንዲያፈርሱ ሲጠይቁ አርሶአደሮች ለማፍረስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ በተነሳ ግጭት ነው ፖሊሶችና አርሶአደሮች የተገደሉት።

በተመሳሳይ ዜና ደግሞ በዋልድባ አካባቢ በምትገኘዋ የዛሬማ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በትናንትናው እለት በርካታ መኪኖችን አግተው ውለዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከወታቶች ጋር በፈጠሩት ግጭት በርካታ ወጣቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከ60 በላይ ወጣቶች መታሰራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኢህአዴግ በዋልድባ ጉዳት ከአባላቱ ጋር ሳይቀር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል። ግንባሩ ያስታጠቃቸው ሚሊሺያዎች ሳይቀሩ በዋልድባ ገዳም ላይ የሚፈጸመውን በደል በመቃወማቸው፣ ግንባሩ ታጣቂ ሚሊሻዎች ትጥቅ እንዲፈቱ አዟል።  በጫራዱቃ  ቀበሌ  8 ታጣቂ ሚሊሺያዎች ብቻ ትጥቅ ሲፈቱ ሌሎች አንፈታም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል። ከዋልድባ ጋር በተያያዘ በአካባቢው ያለው ውጥረት እንዳለ ነው። ሰኔ 21 በሚከበረው የቅድስት ማርያም በአል ላይ ግጭት ሊፈጠር ይችላል በሚል የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ከፍተኛ ቅኝት እያደረጉ ነው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide