በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ

ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከሳስካቺዋን፣ ማኒቶባ እና ከአልበርታ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በሳስካቺዋን ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት በመገኘት ፣ ዩኒቨርስቲው በሙስና እና ዜጎችን በህገወጥ መንገድ በማፈናቀል የሚወነጀሉትን የደቡብ ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን መጋበዙን ተቃውመዋል። ሰልፈኞቹ ዩኒቨርስቲው አቶ ሽፈራውን ወደ መጡበት እንዲመለሱ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ዩኒቨርስቲው የውጭ ጉዳይ ልዩ አማካሪ የሆኑት ቶም ዊሻርት፣ በአቶ ሽፈራው ላይ የቀረበውን አቤቱታ እንዳልሰሙ ነገር ግን ጉዳዩን ለማጣራት እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

አቶ ሽፈራው ወደ ካናዳ ያመሩት በክልሉና በዩኒቨርስቲው መካከል ግንኙነት ለመፍጠር ነው።

የሬጂናው ታየ ሙሉጌታ  “ዩኒቨርስቲው ግለሰቡን መደበቁን ፣ ወደ አካባቢያቸው ተጋብዞ መምጣት የሌለበት መሆኑን” ገልጧል።

የሰብአዊ መብት ተማጓቹ ና የዩኒቨርስቲው ምሩቅ የሆኑት ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “ከአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጋር ምንም አይነት ስራ መስራት የለብንም” ብለዋል።

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ  የአማራ ተወላጆች ከደቡብ ክልል እንዲባረሩ በማድረጋቸው ሲወገዙ ከርመዋል።

ትናንት የተካሄደውን ተቃውሞ ያዘጋጁት ከወቅታዊ የመወያያ መድረክ እና ከቃሌ ፓልቶክ የተውጣጡ አስተዳዳሪዎች ከአካባቢው የኮሚኒቲ ሃላፊዎች ጋር በመተባባር ነው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide